የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ከደቡብ ኢትዮጵያ ከሲዳማ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበራት በሀዋሳ ከተማ መናኸሪያ ክፍለ ከተማ ጉባ ቀበሌ ከአዲሱ ሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስቴድዮም ፊት ለፊት የሚያስገነባው የጋራ ሁለገብ G-6 ህንጻ የተለያዩ የፊኒሽንግ ስራዎች በዘርፉ የተሰማሩ ስራ ተቋራጭ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Teachers Association /EI/ /የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር/ /ኢመማ/
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ከደቡብ ኢትዮጵያ ከሲዳማ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበራት በሀዋሳ ከተማ መናኸሪያ ክፍለ ከተማ ጉባ ቀበሌ ከአዲሱ ሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስቴድዮም ፊት ለፊት የሚያስገነባው የጋራ ሁለገብ G-6 ህንጻ የተለያዩ የፊኒሽንግ ስራዎች በዘርፉ የተሰማሩ ስራ ተቋራጭ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት፡-
- በህንፃ ማጠናቀቅ (finishing contractor) ዘርፍ ወይም ኮንስትራክሽን ማህበራት በህንፃ ስራ ተቋራጭነት BC & GC -9 እና ከዚያ በላይ በዘርፉ 5 ዓመት እና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ ያለው የ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን በሲዳማ ክልል መናኸሪያ ክፍለ ከተማ ሚሊንየም ቀበሌ ከሜሪ ስቶፕ ክሊኒክ ገባ ብሎ አቡነ ጎርጎርዮስ አፀደ ህጻናት ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ወይም አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ከዳሸን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት አለፍ ብሎ በሚገኘው ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ግቢ ከሚገኘው ከማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ባለፈቃዱ ወይም ሕጋዊ ተወካይ አንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በመያዝ መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 /ሃያ ሺ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank guarantee letter/ ከፋይናንሻል ሰነድ ጋር በፖስታ በሰም በማሸግና ማህተም በማድረግ ፈርመው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኛ አቅርበው ሥራውን የሚሠሩበትን የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጅናል፣ ሁለት ፎቶ ኮፒ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶች እንዲሁም የኮንስትራክሽን ማህበሩ ህጋዊነት የሚገልጹ የተሟላ ሰነዶች ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም ሰነዶችን በሌላ አንድ ማጠቃለያ እናት ፖስታ በሰም በማሸግና የማህበሩን ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ተከታታይ በስራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው የውል ማስከበሪያ 10% ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ለመስሪያ ቤቱ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት
- ጨረታው ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የኢመማ የደቡብ ኢትዮ /ሲዳማ/ ማዕከላዊ ኢትዮ /ደቡብ ምዕራብ ኢትዮ መምህራን ማህበር ሀዋሳ በሚገኘው ጂ+6 ሁለገብ ህንፃ ላይ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 5፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ማህበሩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር:- +251 911480257 /924605805 +251 911031038/936731753
+251 916368549/ 924652528 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር
