የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Amhara National Regional Sate Plan And Development Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ)
የዕቃ አቅርቦት ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ግጨ-10/2017
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- በዘርፉ አግባብ ያለው እና የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ለሚገዙ ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 223 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ (ANRS Plan and Development Bureau) በሚል ስም ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ ማለትም ቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በአንድ ፖስታ “ቴክኒካል መመዘኛ” እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሌላ ፖስታ “የዋጋ መወዳደሪያ” የሚል ጽሑፍ በመፃፍ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 001 ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ይታሸግና በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊ ድርጅት የሚመረጠው በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ድርጅት ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 001 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 64 27 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ
