ድርጅታችን ደርባ ትራንስፖርት ኃ.የተ.የግ.ማ ደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግቢ ውስጥ የተለያዩ ያገለገሉ የከባድ ተሽከርካሪ ብዛት ከ3000 በላይ በዓይነታቸው 12x20 እና 12x24 የሆኑት ጎማዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
Derba Transport PLC (ደርባ ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግል ማህበር)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ደርባ ትራንስፖርት ኃ.የተ.የግ.ማ ደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግቢ ውስጥ የተለያዩ ያገለገሉ የከባድ ተሽከርካሪ ብዛት ከ3000 በላይ በዓይነታቸው 12x20 እና 12x24 የሆኑት ጎማዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ ተጫራቾች አስፈላጊውን ማስረጃ በማያያዝ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን የጎማዎቹን ሁኔታ ለማየት ደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካ ጊቢ ውስጥ በመምጣት ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ከ2፡30 – 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 – 10፡00 ሰዓት ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ዋናው መ/ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ በመምጣት የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- በጨረታው መሳተፍ የሚቻለው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ በ3ኛ ፎቅ ሳፕላይ ቢሮ ውስጥ በተዘጋጀው ሳጥን በማስገባት ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የመክፈቻው ቀን ለሥራ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ በድርጅታችን ስም በማዘጋጀት ዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነዱ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የተያዘው ሲፒኦ /CPO/ አሸናፊ ለሚሆነው ተጫራች በዋጋው የሚታሰብለት ሲሆን ለተሸነፉት ግን ተመላሽ ይደረጋል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ
ከመስቀል አደባባይ ወደ ባንቢስ በሚወስደው መንገድ
ኖክ ማደያ አጠገብ ያለው ድል ህንጻ
የስልክ ቁጥር፡ 0115539581
ደርባ ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግል ማህበር
