የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2017 ዓ.ም በጀት አመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል የህክምና መሳሪያ ለአንድ ጊዜ ብቻ እና ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት የህክምና መሳሪያ ጥገና እና ለህሙማን የበሰሉ ምግቦችን አቅርቦት ለአንድ ዓመት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2017 ዓ.ም በጀት አመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል የህክምና መሳሪያ ለአንድ ጊዜ ብቻ እና ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት የህክምና መሳሪያ ጥገና እና ለህሙማን የበሰሉ ምግቦችን አቅርቦት ለአንድ ዓመት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም አግባብነት ያላቸውን ሁሉ በጨረታው እየጋበዝን
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የአቅርቦትና የአገልግሎት አይነት የተዛመደ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ
- የግዥው ወይም የአገልግሎቱ መጠን ከ5000 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሆነ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-4 የተገለፁትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ኦርጅናል ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቃል፡፡
- ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ከሆስፒታሉ ግዥ ክፍል የማይመለስ 200 ብር በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 2% ሲፒኦ ብቻ ከኦርጅናሉ የጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ሙሉ ስምና አድራሻ ጽፎ ማቅረብ ይኖርበታል። በተጨማሪም ኦርጅናል ሰነዱን እና ፎቶ ኮፒ ለብቻው ሙሉ አድራሻው ተጽፎ በጥንቃቄ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታው ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በማስታወቂያ በወጣበት በመጨረሻ የስራ ቀን በ16ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በእለቱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ሆስፒታሉ በሚጋብዘው የቴክኒክ ባለሙያ ተረጋግጦ እቃው/አገልግሎቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ሆስፒታሉ በሚያቀርበው ናሙና እቃው ገቢ ይሆናል፡፡
- አስፈላጊ መረጃ መስጠት ከፈለጉ በሆስፒታሉ ስልከ ቁጥር 0331117670 መደወል ይችላሉ፡፡
ደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
