Tender Detail

Tender Details

  • Company ዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት አክሲዮን ማህበር
  • Address ባሕር ዳር : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 18 32 92 19
  • Website
  • Deadline01 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-01 00:00:00
  • Categories Audio Visual, Photography And Filming Service And Equipment , Camera

የዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት አ/ማ ፎቶ ካሜራ እና ተያያዥ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት አክሲዮን ማህበር


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር AIDSC 02/2017

 

የዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት አ/ማ ፎቶ ካሜራ እና ተያያዥ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
  3. ተጫራቶች የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተቁ. 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ አዲስ አበባ 4ኪሎ አካባቢ በሚገኘው ጽ/ቤታችን አልማ ህንፃ 300 ብር የማይመለስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት አ/ማ ስም በተከፈተው ሒሳብ ቁጥር 1000162587831 በማስገባት እና ባንክ አድቫይስ በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋጋ በመሙላት ማህተምና ፊርማ በመጨመር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለድርጅቱ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በአቅራቢው ስም ለግዥ ፈፃሚ መ/ቤት ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው::
  8. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 20 ተከታታይ ቀናት ሆኖ በ21ኛው ቀን 4:00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. የጨረታ ሰነድ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት እለት ጀምሮ ለ60 ቀናት ይሆናል፡፡
  10. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ 20 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  11. የውል ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ ውሉ ከሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ 30 ቀናት ፀንቶ ይቆያል ።
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ድርጅቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠውን ግዥ 50% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
  14. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 18 32 92 19 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

 

ዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት አክሲዮን ማህበር

ባሕር ዳር

 

Save Tender