Tender Detail

Tender Details

  • Company የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት
  • Address ሰሜን ሸዋ ዞን : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913247806
  • Website
  • Deadline26 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-26 00:00:00
  • Categories Pharmaceutical Products , Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን መንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን ለመ/ቀ/ገ/ወረዳ እንስሳት ሀብት ልማት ተጠሪ ጽ/ቤት በተዘዋዋሪ በጀት 1ኛ የእንስሳት መድሀኒት እና የህክምና እቃ በግልጽ ጨረታ ህጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈጻም ይፈልጋል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን መንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን ለመ/ቀ/ገ/ወረዳ እንስሳት ሀብት ልማት ተጠሪ ጽ/ቤት በተዘዋዋሪ በጀት 1ኛ የእንስሳት መድሀኒት እና የህክምና እቃ በግልጽ ጨረታ ህጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈጻም ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በእንድ ሎት/ ምድብ ያሎት እቃዎች ዋጋቸው ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ የሆኑ እቃዎች ላይ መወዳደር የሚችሉ የቫት ተመዝጋቢ የንግድ ድርጅቶች ብቻ ሲሆኑ ከብር 200.000 /ሁለት መቶ ብር/ በታች የሆኑት እቃዎች ላይ መወዳደር የሚችሉ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑም ያልሆኑም ድርጅቶች የሚወዳደሩ ሲሆን በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ የታደሰ አግባብነት ያለው የንግድ ስራ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነበር/ እና የቫት ተመዝጋቢ ማረጋገጫ ማስረጃ በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ፡፡ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሲሆን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት የሚያቀርቡበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ መሰረት በመሙላት አንድ ኦርጅናል ሰነድ በማሸግ በመ/ቀ/ገ/ወ/ገ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ፡-

  1. ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ መሰረት መሙላት አለበት፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2% ብር ከነቫቱ ማስያዝ አለባቸው።
  3. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 15 ተከታታይ ቀናት ብቻ ሲሆን ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16 ቀን ጠዋት 3፡30 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ወዲያውኑ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  4. ተጫራቾች በሚያርቡት የዋጋ ዝርዝር ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የተሰረዘ ወይም ለማንበብ አስቸጋሪ የሆነ ሰነድ የተከለከለና ከጨረታ የሚያሰርዝ ነው።
  5. ለጨረታ የሚስፈልገውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ ያላቀረቡ ተጫራቾች በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ እና ፖስታው ላይ ስማቸውን ፣ ፈርማቸውን ፣ የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ መሆን አለበት ፡፡
  8. የጨረታ ስርዓቱን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያቸውን በመውረስ ወዲያውኑ ከጨረታ ውጪ ይደረጋሉ፡፡
  9. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ከሆኑ በኋላ የሚያቀርቡት እቃ በጨረታ ሰነድ እስፔስፊኬሽን መሰረት ኦርጅናል እቃ ማቅረብ አለባቸው።
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር - 0913247806/0921747797

 

በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን

 

Save Tender