Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ሀዲያ ዞን ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913609885
  • Website
  • Deadline25 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-25 00:00:00
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles

በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

  1. ሞተር ሳይክሎች የሚገኙበት አድራሻ በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ።
  2. በጨረታው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል፡፡
  3. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም እና የተጫራቾች መመሪያ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ሞተር ሳይክል ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመክፈል በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 14 በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳዳሩበትን ሞተር ሳይክል በተናጠል ወይም በድምር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመነሻ ዋጋ 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
  5. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ መሙያ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታ እንድ ዋና /Original/ እና ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በፖስታ ታሽጎ እንደገና ሁለቱም በአንድ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 14 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሃዝና በፊደል በመጻፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለባቸው ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም፡፡
  7. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሰረት ከአንድ በላይ ሞተር ሳይክል መጫረት ይችላሉ፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው /አስራ ስድስተኛው/ ቀን ከጠዋት 4:00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን ተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  9. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ንብረት አሸናፊነታቸው በደብዳቤ በተገለፀ በ10 /አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው ሆኖም በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ ገዢው ካላነሳ ለሚደርሰው ለማንኛውም ችግር ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  10. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ከመንግስት የሚፈለግ ግብርና ቀረጥ በሻጭ የሚሸፈን ይሆናል።
  11. አሸናፊው ተጫራች ሞተር ሳይክሎች ስም ማዘዋወሪያ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች በሙሉ በአሸናፊው ይሸፈናል፡፡
  12. የተጫራቾች የመነሻ ዋጋ እና የዋጋ ማቅረቢያ የጨረታ ሰነድ አካል ሲሆን ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0913609885 / 0916729418 / 0910512670 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender