በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 14-2017
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በተሽከርካሪዎች ጨረታ እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ማንነቱን የሚገልጽ ማስረጃ (መታወቂያ) ኮፒ በማቅረብ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች ለግልጽ ጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች ዝርዝር እስከ ሰኔ 8/2017 ዓ.ም 6፡00 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 መመልከት ይችላሉ።
- ለግልጽ ጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች የሚጫረቱ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 8/2017 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ 6፡00 የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ እየከፈሉ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ሰኔ 8/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለተሽከርካሪ የሰጡትን ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲፖዚት አካውንት ቁጥር 1000013088865 ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበትን የባንክ አድቫይስ ከጨረታ ሰነዱ እና ከሌሎች መረጃዎች ጋር በማያያዝ በፖስታ የተጫራቹን ስም እና አድራሻ በግልጽ በመፃፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰኔ 9/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ድረስ ቢሮ ቁጥር 506 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል።
- ያስያዙት ዋስትና ለአሸናፊ ተጫራቾች ከሽያጩ ጋር የሚታሰብ ሲሆን በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ባሉት ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለተሽከርካሪ ከሚሰጡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ (15%) የሚጨመር ይሆናል፤ እንዲሁም ተሽከርካሪው ማህበራዊ ታክስ የሚመለከተው ከሆነ የዝዙበትን ዋጋ 3% መክፈል ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉበትን የተሽከርካሪ ዋጋ 5 /በአምስት/ ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ እና ተሽከርካሪውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
- ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ማንሳት ያልቻሉ ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊነታቸው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ዋስትና ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ተሽከርካሪው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
- በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሳጥኑ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ የሰጡትን ዋጋ መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሳቸውን ከጨረታ ውድድር ውጭ ማድረግ አይችሉም።
- በጨረታ ከሚሸጡ ተሽከርካሪ ስመ ንብረት ዝውውር ጋር ተያይዞ ሊኖር የሚችል ማናቸውም ወጪ መ/ቤቱ አይሸፍንም።
- ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- በጨረታ የሚሸጥ ተሽከርካሪ በተቋሙ ከመወረሱ በፊት የተሽከርካሪው አስመጭ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበረ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
- ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች ለግልጽ ጨረታ የወጡ ተሽከርካሪዎችን ከቅ/ጽ/ቤቱ ሰነድ በመግዛት የወጡ የተሽከርካሪዎችን ዝርዝር በመመልከት እንዲሁም በስልከ ቁጥር 058-320-74-18/058-320-75-69 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
አድራሻ፡- በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው ዘመን ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
