ኢትስዊች አ.ማ የተሽከርካሪ ኪራይ (የሰርቪስ አገልግሎት) ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ተሰማርተው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ድርጅቶችን አወዳድሮ በውድድሩ ብቁ ከሚሆነው ድርጅት ጋር ለ1 (አንድ) ዓመት የሚቆይ የውል ስምምነት ማድረግ ይፈልጋል።
Ethswitch S.C (ኢትስዊች አ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ የሃገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ
የተሽከርካሪ ኪራይ (የሰርቪስ አገልግሎት) ግዥ
የጨረታ ቁጥር፦ ETS/NCB/042/2025
ኢትስዊች አ.ማ የተሽከርካሪ ኪራይ (የሰርቪስ አገልግሎት) ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ተሰማርተው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ድርጅቶችን አወዳድሮ በውድድሩ ብቁ ከሚሆነው ድርጅት ጋር ለ1 (አንድ) ዓመት የሚቆይ የውል ስምምነት ማድረግ ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መካፈል የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል።
- በዘርፉ የተሰማሩ እና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ /Tin/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን የቴክኒክ እና የዋጋ ሰነዶቻቸውን ዋና እና ኮፒለየብቻ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ብር ሰላሳ ሺህ) በሲ ፒ ኦ ወይም ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመክፈቻው ሰዓት በፊት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ብር ሁለት መቶ) በመክፈል ከሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ 7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በአስተዳደር መምሪያ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
- የቴክኒክ ሰነዱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡30 ላይ ኮሜርስ ፊት ለፊት፣ ዘመን ባንክ ህንፃ 21ኛ ፎቅ አስተዳደር መምሪያ ይከፈታል።
- ኢትስዊች አማ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኢትስዊች አ.ማ አስተዳደር መምሪያ
ስልክ ቁጥር: +251-11-557-1204/05
ፋክስ: +251-11-557-1115
አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ
