Tender Detail

Tender Details


በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የማይንቀሳቀሱ እና አገልግሎት ሰጥተው ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ ብረታ ብረቶች መስኮቶች በር ፤ አሮጌ ኤጋ እና ኖርማል ቆርቆሮዎች ሻተር አልሙኒየም ስክራፕ የመስኮትና የበር መቃን (ፍሬም)፤ የሻወር ማሞቂያ ቦይለሮች እንዲሁም የሻወር ትሪ በጨረታ አወዳድሮ በኪ.ግ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ል/ቀ/02/2017

 

በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የማይንቀሳቀሱ እና አገልግሎት ሰጥተው ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ ብረታ ብረቶች መስኮቶች በር ፤ አሮጌ ኤጋ እና ኖርማል ቆርቆሮዎች ሻተር አልሙኒየም ስክራፕ የመስኮትና የበር መቃን (ፍሬም)፤ የሻወር ማሞቂያ ቦይለሮች እንዲሁም የሻወር ትሪ በጨረታ አወዳድሮ በኪ.ግ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች

  1. ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ኢሬቻ ማክበሪያ ጎን ወይም ኤሴ በታችኛው በር ፊት ለፊት ሳልኮስት በሚገኘው በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር --- በመምጣት በቅርንጫፉ ሥር በሚገኙ የማይንቀሳቀሱ እና አገልግሎት ሠጥተው ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ ብረታ ብረቶች መስኮቶች በር አሮጌ ኤጋ ቆርቆሮ እና ኖርማል ቆርቆሮዎች ሻተር አልሙኒየም ስክራፕ የመስኮትና የበር መቃን ፤ የሻወር ማሞቂያ ቦይለሮች እንዲሁም የሻወር ትሪ ዝርዝር የያዘውን መረጃ፣የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
  2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚገዙትን ንብረቶች ብቻ የጥቅል ዋጋ እንዲሁም የንብረቱን ዋጋ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ በማሣየት ድምሩን በአሃዝ ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ሥራ በልዩ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የፋይናንስ ገቢ አሰባሰብ ቡድን ቢሮ ቁጥር---በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 8 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ባሉት ጊዜ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ በየምድቡ ከተቀመጡት ዕቃዎች መካከል ተጫራቹ የሚፈልጋቸውን ዕቃዎች ብቻ መርጦ ዋጋ መስጠት አይችልም፤
  3. የዕቃው ንብረቱ /ዋጋ በጨረታ ሠነዱ ላይ ዋጋው፣ የተጨማሪ እሴት ታክሱና ጠቅላላ ድምሩ በሠንጠረዡ መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል፤
  4. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመሥርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፤
  5. ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በታሸገው ኤንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሠነዶቹ ላይ በማስፈር በፊርማ ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፤
  6. ተጫራቾች ለሚገዙት ብረታ ብረቶች፤ ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎች ሻተር አልሙኒየም ስክራፕ እና የሻወር ማሞቂያ ቦይለሮች እንዲሁም የሻወር ትሪ ላይ በጥቅል 6,000.00 / ስድስት ሺህ ብር/ ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ሣጥኑ ውስጥ አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፤
  7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፤
  8. ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም፤
  9. የጨረታ መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፤
  10. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊ እና ተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በኮርፖሬሽኑ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደብዳቤ እንዲገለጽ ይደረጋል፤
  11. ተጫራቾች የጨረታው ውጤቱ በልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  12. በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ በማቅረብ አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው 3 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይደረጋል፤
  13. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ዕቃዎቹን በ5 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፤ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በወቅቱ ካላነሱ የዕቃዎቹን ጠቅላላ ዋጋ 0.001% 1 /1000/ በየቀኑ እየተሠላ በመቀጫነት እንዲከፍሉ ይደረጋል፤ ሆኖም የመቀጫው መጠን የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲደርስ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለቅርንጫፉ ገቢ ተደርጎ አሸናፊነታቸው ይሠረዛል፤
  14. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
  15. ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡት ዋጋ ከማንኛውም ግብር (Taxes) በፊት መሆን አለበት፤
  16. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

 

በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

Save Tender

አዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በሀገር አቀፍና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ በብረት ዘርፍ የተሰማሩ አምራች ድርጅቶች፣ በምርት ግብአት ወይም (Dif...

READ MORE
ድርጅታችን ለሚያከናውናቸው ልዩ ልዩ የግንባታ ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን እና አገልግሎቶችን በቋሚነት የሚያቀርቡ ብቁ አቅራቢዎችን (Suppliers)...

READ MORE