የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ጫጫን ጨምሮ በሁሉም ክ/ከተሞች የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 እንተፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 እና ይህንኑ አዋጅ ለማስፈፀም የአብክመ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ ባወጣው ደንብ ቁጥር 103/2004 በከፍል 3 በአንቀፅ 10 በንዑስ አንቀፅ 1 በፈደል ተራ ከ “ሀ” እስከ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም (ለመኖሪያ፣ ለንግድ፣ ለማህበራዊ አገልግሎት/ የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
የ22ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
- የጨረታው ዙር ... 22ኛ
- የጨረታው አይነት ... መደበኛ
- የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ጫጫን ጨምሮ በሁሉም ክ/ከተሞች የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 እንተፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 እና ይህንኑ አዋጅ ለማስፈፀም የአብክመ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ ባወጣው ደንብ ቁጥር 103/2004 በከፍል 3 በአንቀፅ 10 በንዑስ አንቀፅ 1 በፈደል ተራ ከ “ሀ” እስከ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም (ለመኖሪያ፣ ለንግድ፣ ለማህበራዊ አገልግሎት/ የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ሰው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 ዘወትር በስራ ሰአት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ሁለት የተለያዩ ተመሳሳይ ፖስታዎችን በማዘጋጀት 1ኛ ክፍል ሁለት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን እና ክፍል ሶስት የጨረታ ሀሳብ ማቅረቢያ ሰነዱን 2ኛ ሲፒኦን ሁለቱን ሰነዶች አንዳንድ ኮፒ በማድረግ ኦርጅናሉን ለብቻ ኮፒውን ለብቻ በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግና በፖስታዎቹ ላይ ኦርጅናል ወይም ኮፒ በማለት ለይቶ በመፃፍ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፖስታውን እስከ 10ኛው (አስረኛው) ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 7 ኦርጅናሉን ሰነድ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ኮፒውን ሰነድ ደግሞ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው የሚዘጋው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰአት ላይ ይሆናል፡፡
- ቦታውን መጐብኘት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለፀው መርሃ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው አዳራሽ፡፡ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጧት 4፡00 ሰአት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰአት ላይ ይከፈታል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ እና በመምሪያው ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ እንዲሁም በዌብ ሳይት WWW.mudc.Gov.et ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
