Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ ሰ/ሽዋ ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ፅ/ቤት
  • Address አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 685 0139
  • Website
  • Deadline23 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-23 00:00:00
  • Categories Pharmaceutical Products , Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

በአብክመ ሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ፅ/ቤት ለእንስሳት ጤና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የእንስሳት መድሀኒቶች እና የህክምና መሳሪያዎችን ለመግዛት ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአብክመ ሰ/ሽዋ ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ፅ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2017

 

በአብክመ ሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ፅ/ቤት ለእንስሳት ጤና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የእንስሳት መድሀኒቶች እና የህክምና መሳሪያዎችን ለመግዛት ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ላይ የሚሳተፉ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የስራ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር /1 የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ መረጃዎችን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ ከነቫቱ መሙላት አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የሞሉበትን ጠቅላላ ዋጋ በማስላት ቫትን ጨምሮ የጨረታ ማስከበሪያ 2% ማስያዝ ይኖርባቸዋል ያስያዙበትንም ደረሰኝ ወይም CPO ዋናውን ማቅረብ አለባቸው።
  4. የእያንዳንዱን መድሃኒት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል መሙላትዎን ያረጋግጡ
  5. የዘርፉን ንግድ ፈቃድና የመሳሰሉት መረጃዎች ከኦርጅናል ዶክሜንት ጋር ተያይዘው በፖስታ ታሽገው መቅረብ አለባቸው
  6. በፖስታው በውጪ ገፅ እና በዋጋ መሙያው የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራች ስም ፣ ፊርማና ማህተም ሊኖርው ይገባል።
  7. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  8. በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ላይ የጨረታ መዝጊያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ራሳቸውንከጨረታው ማግለል አይችሉም።
  9. የጨረታ ሰነዱም ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እንስሳት ሀብት ፅ/ቤት ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 100.00/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፤
  10. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከ29/9/2017 እስከ 14/10/2017 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ16ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፅ/ቤታችን ቢሮ ይከፈታል።
  11. ጨረታው ታሽጎ የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓላት ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፣
  12. አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ወይም በጥቅል መ/ቤቱ በሚያወጣው መሰረት ነው፤
  13. ተጫራቾች አሽናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በፅ/ቤታችን በመገኘት የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው፤ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ውል ካልፈፀሙ በግዢ መመሪያው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያውን ውርስ በማድረግ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፤
  14. ተጫራቾች በጨረታ አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጁ መሰረት በተከታታይ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ
  15. ለተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ /ብር ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል እንደተፈፀመ ተመላሽ ይደረጋል።
  16. አሸናፊው ላቀረባቸው መድሃኒቶች እና የህክምና መሳሪያዎች ዋጋ የሚከፈለው በውሉ መሰረት መድሃኒቶችን እና የህክምና መሳሪያዎችን ከፅ/ቤታችን መድሀኒት ቤት ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዞ አጠናቅቆ ገቢ ማድረጉ ሲረጋገጥ ነው፤
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
  18. ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ በስልክ ቁጥር 011 685 0139/ 0601/ 09 13 12 12 92 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በአብክመ ሰ/ሽዋ ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ፅ/ቤት

 

Save Tender