Tender Detail

Tender Details

  • Company የጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address አሶሳ ፡ ቤኒሻንጉልጉሙዝ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 057-44-83-714
  • Website
  • Deadline09 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-09 00:00:00
  • Categories Food And Beverage

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 61 እና 62 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ተይዞ የተወረሰ የምግብ ዘይትን በመጀመሪያ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


 

ለመጀመሪያ ዙር የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የማስታወቂያ ቁጥር  (0017/2017)

 

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 61 እና 62 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ተይዞ የተወረሰ የምግብ ዘይትን በመጀመሪያ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በተገለፀው የጨረታ መስፈርት መሰረት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡-
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30-6፡00 እና ከሠዓት በኋላ 7፡30-11፡00 ሠዓት ቅዳሜ ጠዋት 2፡30 - 6:00 ድረስ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል በጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዘይት የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ዋስትና (CPO) በጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ቅ/ጽ/ቤት ስም በባንክ በተረጋገጠ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ከ26/09/2017 እስከ 02/10/2017 ከጠዋቱ 3፡45 ድረስ አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመምጣት እቃዎቹን ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ጨረታው በቀን 02/10/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  5. የጨረታው መከፈቻ ቦታ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
  6. የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ተጫራቾች ደግሞ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ05 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ ክፍያ ከፈፀሙ በ05 ቀናት ውስጥ እቃዎቹን ተረክበው ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ከላይ በተራ ቁጥር 7 እና 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና እቃዎቹን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ እቃዎቹ በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባሉ፡፡
  10. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ 057-44-83-714 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የአሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender