በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮ/ጉ/ቢሮ አገልግሎት የሚውል ወርክ ስቴሸን /Workstation/ ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮ/ጉ/ቢሮ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮ/ጉ/ቢሮ አገልግሎት የሚውል ወርክ ስቴሸን /Workstation/ ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምዝገባ ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆነው የጊዜ ገደብ የሚገልጽ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ በመያዝ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነድ በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ ስራ ቀናት ውስጥ በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት መ/ኮ/ጉ/ቢሮ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 416 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ የውል ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በማዘጋጀት ኦርጂናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቬሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታ መመሪያ ጋር አባሪ ተደርጎ ተያይዟል።
- ይህ ጨረታ በ10ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- አቅራቢዎቹ የእቃ ዝርዝር ማቅረቢያ ፎርም ላይ ነጠላ ዋጋውን እና ጠቅላላ ዋጋውን እንዲሁም ቀን ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ማሳረፍ ይገባቸዋል። አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ተጫራቾች መመሪያ ባለማክበራቸው የሚፈፀም ማንኛውም ስህተት ሀላፊነቱ የተጫራቾች ይሆናል።
- የአቅራቢዎች ጠቅላላ ዋጋ በቁጥርና በፊደል መጻፊ አለባቸው። በቁጥርና በፊደል በተገለጸው የዋጋ መጠን መካከል አለመመጣጠን ካለ በፊደል የተገለጸው ተቀባይነት ይኖረዋል። በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካል ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል።
- ቢሮ የተሻለ መንገድ ከገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ
4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 416
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮ/ጉ/ቢሮ
