የወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ቡድንና የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ - ሠ በተዘረዘረው መሰረት እንዲሁም በደንብ ቁጥር 103/2004 አንቀጽ 57 ንዑስ አንቀጽ 2 በሊዝ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2005 ለመኖሪያ እና ለንግድ አገልግሎቶች የሚውል ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
የወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ቡድን
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ ቅጽ opm-0005
- የጨረታ ዙር 3ኛ ዙር /2017 ዓ.ም
- የጨረታው ዓይነት /መደበኛ ጨረታ ቁጥር 3/2017
- የወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ቡድንና የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ - ሠ በተዘረዘረው መሰረት እንዲሁም በደንብ ቁጥር 103/2004 አንቀጽ 57 ንዑስ አንቀጽ 2 በሊዝ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2005 ለመኖሪያ እና ለንግድ አገልግሎቶች የሚውል ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
- ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ቦታ በከተማ አስተዳደሩ ፕላን ክልል ውስጥ የሚገኝ ባለ 200 ካሬ ሜትር ሽንሻኖ 2 (ሁለት) ባለ 270 ካሬ ሜትር ሽንሻኖ 1 (አንድ) ቦታ ጠቅላላ ድምር 3 (ሦስት) የመኖሪያ ቦታ 670 ካሬ ሜትር ለጨረታ ተዘጋጅቷል፡፡
- ለንግድ አገልግሎት የሚውል ባለ 759 ካሬ ሜትር ሽንሻኖ 1 (አንድ) ቦታ ባለ 200 ካሬ ሜትር ሽንሻኖ 1 (አንድ) ባለ 127 ካሬ ሜትር 1 (አንድ) 383 ካሬ ሜትር 1 (አንድ) (አራት) የንግድ ቦታዎች በጠቅላላ ድምር 1469.4 ካሜ ለጨረታ ተዘጋጅቷል፡፡
- ማንኛውም የጨረታው አሸናፊ የሆነ አካል ያሸነፈበትን ዋጋ ቅድመ ክፍያ 10% ማነስ የለበትም
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሲያሥገባ 5% በማንኛውም ህጋዊ ባንክ የተጋገጠ ሲፒኦ ወይም በወረኢሉ ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት የገቢ ደረሰኝ የከፈሉበትን ኦሪጅናሉን አያይዘው ማስገባት አለባቸው በጥሬ ገንዘብ ሲፒኦ ማስያዝ የተከለከለ ነው፡፡
- ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሃ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት እና የማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ ጨረታው በአስረኛው ቀን መጨረሻ ከቀኑ 11፡00 ላይ ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 በወ/ከ/አስ/ 01 ቀበሌ አዳራሽ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ አስፈጻሚ ኮሚቴው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ጨረታው በይፋ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በወረኢሉ ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 4 በመገኘት የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ለመኖሪያ 500 /አምስት መቶ/ ብር በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወረኢሉ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ፌስቡክ ድረ ገጽ /ዌብ ሳይት/ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመኖሪያም ይሁን የንግድ ቤት ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ከተመሳሳይ የቦታ ኮድ ውጭ ከአንድ በላይ የጨረታ ሰነድ ኮድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የተጫራቾች የመገምገሚያ መስፈርት በሰነዱ ላይ opm-008 የተገለጸ መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በመ/ቤቱ ስልክ ቁጥር 09 38 84 39 91/ 09 33 51 83 58/ 09 20 18 57 93 ላይ በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል
የወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ቡድን
