በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት ከሃምሌ 01/2017 እስከ ሰኔ 30/2018 ድረስ የሚቆይ የተለያዩ አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ መሰረት አወዳድሮ መግዛት ወይም ማሰራት ይፈልጋል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት ከሃምሌ 01/2017 እስከ ሰኔ 30/2018 ድረስ የሚቆይ የተለያዩ አገልግሎቶች ማለትም፦
- ሎት 1. የጽዳት አገልግሎት /Out source/
- ሎት 2. የሰራተኞች የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት
- ሎት 3. የደረቅ ጭነት አገልግሎት
- ሎት 4. የመኪና ጥገና አገልግሎት
- ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ መሰረት አወዳድሮ መግዛት ወይም ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር tin ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታ ሰነዱን በብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ግ ፋይ ንብ አስደ የስ ሒደት ቢሮ መውሰድ ይቻላል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ያስገቡትን ጠቅላላ ዋጋ 1% ያክሉን ለሆስፒታሉ በCPO በመሂ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።
- ከብር 3000 /ሶስት ሺህ ብር በላይ ለሚገዙ አገልግሎቶች 2% የመቁረጥ እና በሥማቸው የታተመ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊ ሆኖ የሚገባው ተጫራች የፅዳት አገልግሎቱን ለ24፡00 ሰዓት ሳይቆራረጥ መስጠት አለበት። በመሆኑም የፅዳት ቋሚና አላቂ ግብአቶች በወሩ መጀመሪያ 1-3 ባሉት ቀናት ውስጥ ማስገባት አለበት።
- የሰራተኛ ሰርቪሱ 28 ወንበርና ከዚያ በላይ ያለው ደረጃ አንድ ቅጥቅጥ መሆን አለበት።
- የተሽከርካሪው የስምሪት ዘመን የቅርብ ጊዜ የሆነ አዲስ ሞዴል መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ለመኪናው የሚያስፈልጉ የተለያዩ ወጪዎች እና የናፍታ ከፍያ በራሱ በተጫራቹ ነው።፡፡
- ተሽከርካሪው ሙሉ ቀን ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚሠጥ/መስጠት የሚችል መሆን አለበት።
- የተሽከርካሪው ሊብሬ በተጫራቹ ስም የሆነ ኢንሹራንስ እና ሶስተኛ ወገን የተገባለት እንዲሁም የቴክኒክ ምርመራ /ቦሎ/ ያሰራ መሆን አለበት።
- ተሽከርካሪው በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የተመዘገበ መሆን አለበት።
- ለሁሉም ሎቶች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ሙሉ አድራሻቸውን ሥማቸውን ፊርማቸውን እና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው።
- አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበሪያ 10% ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ በ CPO በማስያዝ ውል መውሰድ የሚችል መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ዝርዝር አባሪ ዶክመንቶችን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡00 ላይ ይከፈታል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ እና ሠዓት ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት በሆስፒታሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግድም።
- ለሁሉም ሎቶች ተጨማሪ መረጃዎችን ከጨረታው መመሪያና ከዋጋው መሙያ ላይ ማግኘት ይቻላል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ /ዝግ ከሆነ በቀጣዩ ባለው የሥራ ቀናት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በሥልክ ቁጥር 09 20 20 56 42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡- በደሴ መስመር በሚወስደው አስፋልት ከሸዋሮቢት ከተማ 3 ኪሎ ሜትር አለፍ ብሎ ወደ ምእራብ 500 ሜትር ገባ ብሎ እንገኛለን።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
