Tender Detail

Tender Details


የደ/ ምዕ ኢት/ሕ ክ/ መንግስት በከፋ ዞን ከጨና ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በየሴክተሩ በተለያዩ ምክንያቶች ተበላሽተው ሳያገለግሉ ቆመው የቆዩ ተሽከርካሪዎችንና የተለያዩ አገልግሎት የማይሰጡ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እንደየደረጃቸው ግልጽ ጨረታ አውጥቶ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችና ኤሌክትሮኒክሶችን ለመሸጥ

የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁ/2/ 2017 ዓ.ም

 

የደ/ ምዕ ኢት/ሕ ክ/ መንግስት በከፋ ዞን ከጨና ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በየሴክተሩ በተለያዩ ምክንያቶች ተበላሽተው ሳያገለግሉ ቆመው የቆዩ ተሽከርካሪዎችንና የተለያዩ አገልግሎት የማይሰጡ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እንደየደረጃቸው ግልጽ ጨረታ ወጥቶ እንዲሸጥ በባለሙያዎች ተለይተው እንዲቀርቡ በተጠየቀው መሰረት መሸጥ ያለባቸውን ተሽከርካሪዎችና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ለይተው በደ/ቁ 760/01-04 በ 26/07/2017 ዓ.ም ያቀረቡ በመሆኑ የጨና ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ ጽ/ቤትም ይህን ተከትሎ በደ/ቁ/2564/27-150/2017 በ 14/08/2017 ዓ.ም ኮሚቴው ባቀረበው መነሻ ዋጋ መሰረት በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ወጥቶ እንዲሸጥ በተጻፈው ደብዳቤ መሰረት፡-

  • ሎት 01 የተለያዩ ያገለገሉ መኪናዎች፣ ትራክተሮች፣ ሞተር ሳይክልና የመሳሰሉት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 20,000.00(ሃያ ሺህ)
  • ሎት 02 የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክሶች በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 10,000 (አስር ሺህ)

ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ21 ቀናት ጨረታው በአየር ላይ ስለሚውል የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ/ ሰነዱን ከጨና ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ ቢሮ ቁ 03 ቀርባችሁ በመግዛት በማንኛውም የስራ ቀናት በተሰጠው መነሻ ዋጋ ላይ ጨምራችሁ በፖስታ አሽጋችሁ ፊርማ በመፈረም ጨና ወረዳ ፋይ ኢ/ል/ጽ/ ቤት ቢሮ ቁ3 ድረስ በመምጣት ለሱ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እንድታስገቡ እናሳውቃለን ። ጨረታው በ22ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ5፡00 ሰአት ይታሸጋል፡፡ በእለቱ 5፡30 ሰአት ህጋዊ ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች ያለመኖር የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ እንደታወቀ ያሸነፈበትን ዋጋ ከፍሎ ንብረቱን ይረከባል፡፡ አሸናፊነቱ ከታወቀ እስከ 10 ቀን ድረስ ንብረቱን ባይረከብ ያስያዘው ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ ለወደፊትም እንደዚህ አይነት ጨረታና በመሳሰሉት እንዳይሳተፍ ይደረጋል። ፖስታውን ስታስገቡ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ ከተቁ 1-2 ድረስ በተመዘገበው መሰረት ሎት1ና 2ትን በባንክ በተረጋጋጠ ሲፒኦ ጋር ለየብቻ አያይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባችኋል።

የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች ነው፤

ማሳሰቢያ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ ጨና ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመቅረብ ስለሰነዱ ሁኔታ መጠየቅ ትችላላችሁ፡፡ የምትወዳደሩበትን እቃ አድራሻ በምትገዙት ሰነድ ላይ ስላለ በአካል እስከቦታው ሄዳችሁ ማየት ትችላላችሁ።

 

የደ/ምዕ/ኢት/ሕ/ክ/ መንግስት በከፋ ዞን ከጨና ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

 

Save Tender