Tender Detail

Tender Details


የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ያገለገሉ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

Space science and Geospatial Institute (SSGI) (የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት)


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ብ/ግ/ጨ/SSGI/01/2017

 

የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ያገለገሉ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት

  1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይስህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ ግዢ ሲመጡ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል በኢንስቲትዩቱ ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ ቢሮ ቁጥር 1-15 ድረስ በመምጣት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

 

ተ.ቁ

የሚፈፀመው ሽያጭ

መግለጫ

1

ኤሌክትሮኒክስና የቢሮ መገልገያዎች

ሎት 1

2

የመኪና ጎማና ባትሪ

ሎት 2

3

አሮጌ የቅየሳና አጋዥ መሳሪያዎች

ሎት 3

 

  1. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ የሚኖርበት ሲሆን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በኢንስቲትዩቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
  2. የጨረታ መክፈቻ ቀን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከ10 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የመጀመሪያ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጠለው የስራ ቀን ይሆናል።
  3. ተጫራቾች ለግልጽ ጨረታ ለሚጫረቱባቸው እቃዎች የመነሻ ዋጋ አስር በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንደ አስፈላጊነቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-

አዲስ አበባ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጎን በሚገኘው የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና መ/ቤት ቅጥር ግቢ ኮርስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1-15 ገንዘብ ቤት ነው።

የስልክ ቁጥር፡- 011-872-0286

 

በኢፌዴሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት

 

Save Tender