Tender Detail

Tender Details

  • Company የባቲ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
  • Address ባቲ ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline10 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-11 00:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የባቲ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት 8 (ስምንት) የከተማ መሬት ልማት ቡድን ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል ቦታ እና 3 (ሶስት) ለድርጅት/ንግድ የሚውል ቦታ እንዲሁም 11 (አስራ አንድ) ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

የባቲ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት


 

የ2017 የ1ኛ ዙር መደበኛ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

 

  1. የባቲ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ መሬት ልማት ቡድን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1  በፊደል ተራ ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት 8 (ስምንት) ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል ቦታ 1526.46 (አንድ ሺ አምስት መቶ ሀያ ስድስት ነጥብ አርባ ስድስት) ካ/ሜ ስፋት እና 3 (ሶስት) ለድርጅት/ንግድ የሚውል ቦታ 1,015.28 (አንድ ሺ አስራ አምስት ነጥብ ሀያ ስምንት ካሜ ስፋት በጠቅላላ 2,5474 (ሁለት ሺ አምስት መቶ አርባ አንድ ነጥብ ሰባ አራት ካሬ ሜትር ስፋት የተዘጋጀ 11 (አስራ አንድ) ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መሠረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከቀን 19/09/2017 ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 250 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር ብቻ በመከፈል በባቲ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የባቲ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ አዳራሽ ጎን UIDP ቢሮ በስራ ሰዓት በአካል በመቅረብ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከ 9/09/17 እስከ 03/10/2017 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል፡፡
  3. ቦታውን መጎበኘት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሀ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል።
  4. ጨረታው የሚዘጋው 03/10/2017 ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይሆናል።
  5. ጨረታው የሚከፈተው በ04/10/2017 ከቀኑ 03:00 ሰዓት በባቲ ከተማ ማዘጋጃ አዳራሽ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።
  6. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወይም በባቲ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽቤት የባቲ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ አዳራሽ ጎን UIDP ቢሮ በስራ ሰዓት በአካል በመቅረብ ማግኘት ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ፡ መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የባቲ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

 

Save Tender