Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ
  • Address ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0462121127
  • Website
  • Deadline10 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-10 00:00:00
  • Categories Vehicle

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ያገለገሉ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ


 

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/ 2017

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ያገለገሉ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙባቸው አድራሻዎች

  1. በሲዳማ ብ/ክ/መ/ ሀዋሳ ከተማ ከፖስታ ቤት አጠገብ በአሁኑ ሰዶማ ልማት ማህበር ጽ/ ቤት ግቢ ውስጥ፤
  2. ከቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ጀርባ በሲዳማ ብ/ክ መ/ ት/ቢሮ ግቢ ውስጥ፤
  3. በቀድሞው ሲ/ብ/ክ/መ ጤና ቢሮ ግቢ ውስጥ ከሀዋሳ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ጎን፤
  4. ከሀዋሳ አሮጌ መናኸሪያ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው በሲዳማ ብ/ክ/መ/ ገቢዎች ቢሮ ግቢ ውስጥ
  5. በሲዳማ ሰሜናዊ ዞን ቦርቻ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ይርባ ከተማ እና ቦርቻ ወረዳ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት ይርባ ከተማ፤
  6. በሲዳማ ደቡባዊ ዞን አለታ ጩኮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የሚገኙ ሲሆን፤
  7. በቀድሞው ወሳኝ ኩነት ግቢ ውስጥ ከሀዋሳ አሮጌ መናኸሪያ 150 ሜትር ገባ ብሎ።

 

  1. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸውን ከማቅረባቸው በፊት ያገለገሉ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአካል በመገኘት ከላይ በተገለፁት አድራሻዎች አስቀድመው ማየት እና ከተመለከቱ በኋላም ከጨረታ ሰነዱ ጋር ልዩነት መኖሩን ሲያረጋግጡ ጨረታው ከመዘጋቱ ከአምስት የሥራ ቀናት በፊት ለአገልግሎቱ ማሳወቅ አለባቸው፡፡ ይህን ሳያደርጉ የቀሩ ተጫራቾች ጨረታው ከታሸገ በኋላ ለሚያቀርቡት አቤቱታ መ/ቤቱ ምላሽ ለመስጠት አይገደድም።
  2. በጨረታው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል።
  3. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ሰነዱን ለመግዛት ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ኦርጅናልና ኮፒ ይዞ በአካል መቅረብ ይኖርበታል።
  4. በውክልና ሰነድ ለመግዛት የሚፈልጉ አካላት በውልና ውክልና ማስረጃ የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ እና የወካዩን መታወቂያ ይዘው በአካል መቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሽከርካሪ የሚገዙበትን የጨረታ መግዣ ጠቅላላ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (cpo) በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ስም በማቅረብ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
  6. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድሩ ቢወጡ ለጨረታው ማስከበሪያው ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  7. የአሸናፊዎች ዝርዝር በማስታወቂያ ሠሌዳ እንደተገለፀ ወዲያውኑ ጨረታውን ላላሸነፉ ተጫራቾች CPO ተመላሽ ይደረጋል።
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን ለመረከብ በቅድሚያ የሲፒኦ ኮፒ፣ እንዲሁም ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ተወካይ ከሆነ በውል እና ማስረጃ የተረጋገጠ ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  9. ተጫራቾች በአንድ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ከአንድ በላይ ተሽከርካሪ መጫረት አይችሉም።
  10. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን የተሽከርካሪዎች ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በቢሮው የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 301 የማይመለስ 500 ብር በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  11. ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በሚታይ በአኃዝ እና በፊደል በመጻፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለበት፡፡ በአኃዝ የተጻፈውን ለማንበብ የሚያዳግት ከሆነ በፊደል የተጻፈው የሚገዛን ይሆናል።
  12. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የእያንዳንዱን ተሽከርካሪ ንብረት ዋጋ በአንድ ኦርጂናልና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ከጠዋቱ 4፡00-ሰዓት ድረስ በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 301 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  13. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 7፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ የሚከፈት ሲሆን ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የደረሰ ተጫራች ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት አይስተጓጎልም፤
  14. የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል ቅዳሜ ወይም እሁድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
  15. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪዎችን ሙሉ ክፍያ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ያሸነፉትን ንብረት ማንሳት አለባቸው በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ለ30 ተከታታይ ቀናት የንብረቱ ዋጋ 0.2% በየቀኑ የቦታ ኪራይ እየታሰበ የሚከፍል ሲሆን በዚህም ጊዜ ገደብ ንብረቱን ማንሳት ካልቻለ ያስያዙት CPO ለመንግስት ውርስ ሆኖ ለንብረቱ ድጋሚ ጨረታ ወጥቶ የሚሸጥ ይሆናል።
  16. መ/ቤቱ የጨረታ ሰነዱ መስተካከል አለበት ብሎ ሲያምን ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት በማንኛውም ጊዜ የጨረታ ሰነዱን ማስተካከል የሚችል ሲሆን ይህንንም ለሁሉም ተጫራቾች በማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ እና በሥልክ እንዲሁም በፋይናንስ ቢሮው ዌብ ሳይት በግልፅ ያሳውቃል፤
  17. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪዎች የስም ማዛወሪያ እና ማንኛውንም ተሽከርካሪውን የሚመለከት ሙሉ ክፍያ በራሳቸው ወጪ የሚሸፍኑ ይሆናል፡፡
  18. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 212 0115 መደወል ይቻላል።

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ

 

Save Tender