በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አስተዳደር የባልጭ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በባልጭ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ጠቅላላ ስፋቱ 450 ካሬ ሜትር የሆነ ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የባልጭ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት
የመጀመሪያ ዙር የመሬት ሽያጭ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አስተዳደር የባልጭ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በባልጭ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ጠቅላላ ስፋቱ 450 ካሬ ሜትር የሆነ ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ ስመሳተፍ ፈቃድኛ የሆኑ ተጫራቾች፡-
- የጨረታውን ሰነድ በባልጭ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ የኢትዮ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ቦታው የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታውን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን /Specification/ መሰረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 10 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ10 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በአ/ብ/ዞን በባልጭ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ከ20/09/2017–04/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡ዐዐ ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ4/10/2017 ዓ.ም በ11፡00 ሰዓት ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ5/10/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት በባልጭ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ቦታውን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት በባልጭ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በሚመድባቸው አስጎብኚዎች ቦታዎቹን መመልከት ይችላሉ።
- የአካበቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ በባልጭ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ።
- የባልጭ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፡- 09-19-96-70-28/ 09-21-03-19-11 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የባልጭ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት
