Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline25 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-25 00:00:00
  • Categories Food And Beverage

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (onboard service) እና ለስካይላይት ሆቴል አገልግሎት የሚውል የተጣራ ማር አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ የሦስት (3) ዓመት ውል በመግባት አብሮ ለመስራት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: -SSNT-T541

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (onboard service) እና ለስካይላይት ሆቴል አገልግሎት የሚውል የተጣራ ማር አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ የሦስት (3) ዓመት ውል በመግባት አብሮ ለመስራት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

  1. በአገልግሎቱ ዘርፍ ለመሠማራት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ ለ2017 ዓ.ም. የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የ ግብር ከፋይ ምዝገባ ወረቀት ያለው (TIN)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ (VAT)፣ አንድ (1) ዓመት እና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ ያለው ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
  2. ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (ብር 100.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T541 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
  4. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ሦስት መቶ ሺህ ብር (300,000.00ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ውስንነት ያለው (Conditional) የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
  5. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ሰኔ 18 ቀን 2017 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

ስልክ ቁጥር፡ 011-517-8953

ኢ-ሜይል: TeymeT@ethiopianairlines.com

 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

Save Tender