የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአፈጻጸም ተከሳሽ ስም የሚገኘውን የአቀማመጥ አቅጣጫው በምዕራብ ጀማል ላምሶ በምስራቅ መንገድ በሰሜን ተፍራ ከበዴ እና በደቡብ በላይነህ ለገሠ በተባሉት መካከል ተከብቦ የሚገኘውን ቤት እና ቦታ ፍርድ ቤቱ በጨረታ እንዲሸጥ አዟል። ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የአፈጻጸም ከሳሽ፡- አቶ ሙሉጌታ ዱካሞ ቡና ላኪ የግል ድርጅት እና የአፈጻጸም ተከሳሽ፦ አቶ ግርማ ጮካ የተባለው መካከል ስላለው የፍትሐብሔር አፈጻጸም ገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በተመለከተ የአፈጻጸም ተከሳሽ የሆነ ቤት ዳዬ ከተማ 01 ቀበሌ ውስጥ የሚገኘው የፕላን ቁጥር 377 የሆነ የአፈጻጸም ተከሳሽ እንዲከፍል ፍርድ ቤቱ የተሰጠው ውሳኔ የዕዳ ገንዘብ 610,000 (ስድስት መቶ አስር ሺህ) ብር በአፈጻጸም ተከሳሽ ስም የሚገኘውን ቤት የአቀማመጥ አቅጣጫን በተመለከተ በምዕራብ ጀማል ላምሶ በምስራቅ መንገድ በሰሜን ተፍራ ከበዴ እና በደቡብ በላይነህ ለገሠ በተባሉት መካከል ተከብቦ የሚገኘውን ቤት እና ቦታ ፍርድ ቤቱ በጨረታ ሸጦ ለአፈጻጸም ከሳሽ ስለሚያስከፍል ዳዬ ከተማ ማዘጋጃ ጽ/ቤት የቤት እና ቦታ የጨረታ መነሻ ዋጋ 1,262,520.76 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ስልሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሃያ ብር ከሰባ ስድስት) ሳንቲም ይሆናል ብሎ በገመቱት መሠረት ተጫራቾች ከመነሻ ዋጋ በላይ አቅርበው በጨረታ መግዛት የሚፈልግ የጨረታ ሰነድ የዚህ ፍ/ቤት ግዥና ክፍያ ቢሮ ቁጥር 3 ቀርበው የጨረታ ሰነድ ተቀብሎ ለውድድር በመቅረብ ጨረታውን አሸንፎ የሚገዛ በቀን 03/10/2017 ዓ.ም እንደሚገዛ እና ጨረታው የሚከፈትበት ቀን 4/10/2017 ዓ.ም ህጋዊ ውክልና ያላቸው ተወካዮች ተጫራቾችና የጨረታ ኮሚቴ ባሉበት ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት በይፋ ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል እንደሚሰረዝ ያሳውቃል።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
