የኢትዮጵያ ዓይነሥውራን ብሔራዊ ማኅበር ሰብሬሎ 300 እና 600 የብሬል ጽሁፍ ማተሚያ ማሽን የሚሆን የብሬል ወረቀት ማለትም ከ140-150 GSM የሆነ በግራ እና በቀኝ ህዳግ ከማተሚያ ማሽኑ ጋር ለማሠር የሚያስችሉ ቀዳዳዎች ያሉት፣ 19 የሸንበቆ ወይም የሪንግ ማስገቢያ ያለው፣ ሳይዝ 12.5 x የሆነ እና 12,000 ካርቶን ወይም ሳጥን ባለ 1,000 የተያያዘ ወረቀት ወይም continuous sheet የብሬል ወረቀት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ዓይነስውራን ብሔራዊ ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ዓይነሥውራን ብሔራዊ ማኅበር ሰብሬሎ 300 እና 600 የብሬል ጽሁፍ ማተሚያ ማሽን የሚሆን የብሬል ወረቀት ማለትም ከ140-150 GSM የሆነ በግራ እና በቀኝ ህዳግ ከማተሚያ ማሽኑ ጋር ለማሠር የሚያስችሉ ቀዳዳዎች ያሉት፣ 19 የሸንበቆ ወይም የሪንግ ማስገቢያ ያለው፣ ሳይዝ 12.5 x የሆነ እና 12,000 ካርቶን ወይም ሳጥን ባለ 1,000 የተያያዘ ወረቀት ወይም continuous sheet የብሬል ወረቀት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፦
- በዘርፉ የ2017 የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይነት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት መለያ ቁጥር ፤ በጨረታዎች ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚያሳይ የጸና የምስክር ወረቀት ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 200.00 ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከማኅበሩ ዋና ጽ/ቤት በአካል ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ 500,000.00 ብር CPO ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ሰነዶች ኦሪጅናል እና ቅጂዎችን ለየብቻ በማሸግ በአንድ ፖስታ አድርገው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድም እንዲሁ ለብቻው ታሽጎ ከሌሎች ሰነዶች ላይ መቅረብ አለበት፡፡
- ድልዝ ስርዝ ያለበት ማንኛውም ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የአንዱን ካርቶን ወረቀት እና ጠቅላላ ዋጋ በግልጽ፣ በአሀዝ እና በፊደል ማመልከት ይኖርባቸዋል።
- ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
የኢትዮጵያ ዓይነስውራን ብሔራዊ ማህበር
