በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን የማንድራ ወረዳ መስተዳደር ጽ/ቤት በገ/ማርያም ከተማ /በወላንባ ቀበሌ ለወረዳው ጠቅላላ የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ቢሮ በግልጽ ጨረታ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የማንድራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን የማንድራ ወረዳ መስተዳደር ጽ/ቤት በገ/ማርያም ከተማ /በወላንባ ቀበሌ ለወረዳው ጠቅላላ የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ቢሮ በግልጽ ጨረታ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የማ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ GC-4/BC-4 እና ከዚያ በላይ ደረጃ ያላቸው ተጫራቾች:-
- የ2017 ዓ ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ኮፒ ማቅረብ የሚችል
- የቫት (የተጨማሪ እሴት ታከስ) ተመዝጋቢ የሆነበት ኮፒ ማቅረብ የሚችል፣
- የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ የሚችል፣
- የ2017 ግብር ስለመከፈላቸው የታክስ ክሊራንስ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፣
- የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
- የብቃት ማረጋገጫ ደረጃ GC-4/BC-4 እና ከዛ በላይ ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
- በድርጅቱ ከዚህ በፊት የተሰሩ ስራዎች 10,000,000 የ3 ዓመት አማካይ የሽያጭ መጠንና የባንክ የሂሳብ እንቅስቃሴ ማቅረብ የሚችል
- ጽ/ቤቱ ቅድም ከፍያ (Advance Payment) የማይከፍል መሆኑን በመረዳት በራስ አቅም ስራውን በውሉ መሠረት እያከናወነ ክፍያ የሚጠይቅ የሚችል፣
- ዝርዝር የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ግልገል በለስ ከተማ በሚገኘው የማንድራ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 09 ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል በመቅረብ የማይመለስ 1000 ብር /አንድ ሺህ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 21 (ሃያ አንድ ቀናት) ሲሆን ግልገል በለስ ከተማ በሚገኘው ማንድራ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በሃያ ሁለተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡45 ሠዓት ታሽጎ በዛው እለት ከጠዋቱ 4፡15 ሠዓት የሚከፈት ይሆናል፤ እለቱ በዓል ወይም እሁድ፣ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒዎች እያንዳንዳቸውን በሰም ታሽጎ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ ውስጥ በማስገባት እንዲሁም ለ30 መቁጠሪያ ቀናት የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በ(CPO) ከባንክ ማቅረብ የሚችልና ከኦርጅናል ቴክኒካል ዶክመንት ጋር በማድረግ ፖስታው ላይ ቴክኒካል በሚል ፊርማና ማህተም በማድረግ ተለይቶ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት የሚችል፡፡
- ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በሰም በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ፖስታው ላይ ፋይናንሻል በሚል ተለይቶ በፖስታው ላይ ፊርማና ማህተም በማድረግ በመለየት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ ለማንድራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ስም መሰራት አለበት።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መከፈቻው ቀን ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ኮሚቴው ጨረታውን የመከፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ስለስራው አይነትና መጠን ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ከጨረታ መክፈቻ ቀን 07 /ሰባት ቀን አስቀድሞ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለመስክ ምልከታ በራሳቸው ወጪ ግንባታው ቦታ ድረስ በመሄድ ማየት ይችላሉ፡፡
- የዋጋ መሙያው ሰነድ ስርዝ ድልዝ ያለበት ከሆነ ፓራፍ የማድረግ ግዴታ አለባቸው ካልሆነ ግን የጨረታ ኮሚቴው ውድቅ ለማድረግ ይገደዳል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጡ ቴክኒካል መመዘኛዎችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፤ ከዚህም በተጨማሪ ቴክኒካል መስፈርት የማያሟሉ ተጫራቾች ያቀረቡት ፋይናንሺያል ሰነዱ አይከፈትም፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ሌሎች በማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ መስፈርቶች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጨረታ አሰራሩን በተመለከተ በአገሪቱ የግዥ መመሪያ ይዳኛል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር +251-920-89-56-87 መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
የማንድራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
