አዲስ ጉዞ የድርጅቱ ንብረት የሆኑ እና ያገለገሉ ሰባት (7) ኮንቴነሮች (20 foot sheeping containers) ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለግለሰቦች ወይንም ለድርጅቶች በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
አዲስ ጉዞ
የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ ጉዞ የድርጅቱ ንብረት የሆኑ እና ያገለገሉ ሰባት (7) ኮንቴነሮች (20 foot sheeping containers) ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለግለሰቦች ወይንም ለድርጅቶች በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 05 የወጣት ማዕከል ፊት ለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ በመገኘት ዝርዝር የጨረታ ጉዳዮችን የያዘ የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ሰባት (7) ኮንቴነሮች (20 foot sheeping containers) በልደታ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ልደታ ፀበል ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በሚገኘው የአካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ልማት ማዕከል ግቢ ውስጥ በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ያሉ መስፈርቶችን በማሟላት እና ዝርዝር ጉዳዮችን ያለስረዝ ድልዝ በግልፅ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ድርጅቱ ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 09፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡
- ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በመግለፅ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ መፈረም የሚኖርባቸው ሲሆን ይህንኑ አድራሻቸውን የሚገልፅ ህጋዊ ሰነድ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው።
- ለጨረታ የቀረቡት ስድስት ባለ 20 foot ኮንቲነሮች የኮንቴነር አገልግሎት የሰጡ ሲሆን ተጫራቾች የሚያስገቡት የጨረታ ዋጋ በዚሁ አግባብ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት በኮንቲነሮቹ ሁኔታ መሰረት ተለይቶ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
- ለስድስቱ ባለ 20 foot የኮንቴነር አገልግሎት የሰጡ ኮንቴነሮች ተጫራቾች ለመግዛት የሚያቀርቡት ዝቅተኛ የኮንቴነር ብዛት 6 (ስድስት ሲሆን) መስኮትና በር የተገጠመለት ለተገጠመለት ባለ 20 foot ኮንቴነር የተናጠል ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ያስገቡትን ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በአዲስ ጉዞ ድርጅት ስም አሰርተዉ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታዉ ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛዉ የስራ ቀን ላይ ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግቢ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታ አከፋፈቱ አይስተጓጎልም፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማራሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0941145202 በመደወል ወይንም በአካል በመገኘት መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
አዲስ ጉዞ
