በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤት አገልግሎት ሰጥተው ተመላሽ የተደረጉና አዲስ አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ የቢሮ፤ የግንባታ፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ የኤሌክትሪክ፤ የደንብ ልብስ፤ ብረታብረት እና በእዳ ምክንያት የተወረሱ እቃዎችን በየመጋዘኑ የሚገኙ የቤት ውስጥ ቁሳቁስ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የቅርንጫፍ ሁለት ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ቅ/2/09/2017
በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤት አገልግሎት ሰጥተው ተመላሽ የተደረጉና አዲስ አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ የቢሮ፤ የግንባታ፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ የኤሌክትሪክ፤ የደንብ ልብስ፤ ብረታብረት እና በእዳ ምክንያት የተወረሱ እቃዎችን በየመጋዘኑ የሚገኙ የቤት ውስጥ ቁሳቁስ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- በመስኩ ህጋዊ የዘመኑ ወይም የታደሰ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ቄራ ከአርባምንጭ ዓሣ ቤት አለፍ ብለው ሳንቴ የህክምና ማዕከል ፊት ለፊት በሚገኘው በቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፋይናንስና ገቢ አሰባሰብ ቡድን ቢሮ በመምጣት በቅርንጫፉ ሥር በሚገኙ አገልግሎት ሠጥተው ተመላሽ የተደረጉና አዲስ አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ የቢሮ፤የግንባታ፤ የጽህፈት፤ኤሌክትሪክ፤የደንብ ልብስ፤ብረታብረት እና በእዳ የተያዙትን እቃዎችን ዝርዝር የያዘውን መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር ከፍለው መግዛት ይኖርባቸዋል።
- በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚገዙትን ንብረቶች ዝርዝር ዋጋ እንዲሁም የንብረቱን ዋጋ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ በማሣየት ድምሩን በአሃዝ ያለስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ሥራ በቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ በየምድቡ ከተቀመጡት ዕቃዎች መካከል ተጫራቹ የሚፈልጋቸውን ዕቃዎች ብቻ መርጦ ዋጋ መስጠት አይችልም።
- የዕቃው /ንብረቱ/ ዋጋ በጨረታ ሠነዱ ላይ ዋጋው ፣የተጨማሪ እሴት ታክስና ጠቅላላ ድምሩ በሠንጠረዡ መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመሥርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በታሸገው ኢንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሠነዶቹ ላይ በማስፈር በፊርማ ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚገዙበትን ጠቅላላ ዋጋ 15% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ 2 ፅ/ቤት በሚል (CPO) በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ሣጥኑ ውስጥ አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ
- ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤት የሰራተኛ መዝናኛ ክበብ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
- ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሠዓት በኃላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ ሠሌዳና በደብዳቤ እንዲገለጽ ይደረጋል።
- ተጫራቾች የጨረታው ውጤቱ በቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤት የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ በማቅረብ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ7 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይደረጋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ዕቃዎቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፤ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በወቅቱ ካላነሱ የዕቃዎቹን ጠቅላላ ዋጋ 0.001% /1/1000/ በየቀኑ እየተሠላ በመቀጫነት እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡ ሆኖም የመቀጫው መጠን የጠቅላላውን ዋጋውን 10% ሲደርስ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለቅርንጫፉ ገቢ ተደርጎ አሸናፊነታቸው ይሠረዛል፤
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች 011-115-45-49 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
- ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡት ዋጋ ከማንኛውም ግብር (Tax) በፊት መሆን አለበት።
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የቅርንጫፍ ሁለት ጽ/ቤት
