Tender Detail

Tender Details


እድገት ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ለሚሰራቸው ስራዎች የህንጻ መሳሪያ፣ የኤሌክትሪክ እቃ፣ የእግረኛ መንገድ የመብራት ፖል፣ የሳኒተሪ እቃ፣ ደስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ፣ ጠረጴዛ፣ ወንበር፣ የአስፋልት ማርኪንግ የተለያዬ ቀለም ማቅረብና በማሽን መቀባት፣ አልሙኒየም ማቅረብና መገጣጠም፣ የተፈጨ ጠጠር፣ የግንብ ድንጋይ እና አሸዋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

እድገት ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2017

 

እድገት ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ለሚሰራቸው ስራዎች የህንጻ መሳሪያ፣ የኤሌክትሪክ እቃ፣ የእግረኛ መንገድ የመብራት ፖል፣ የሳኒተሪ እቃ፣ ደስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ፣ ጠረጴዛ፣ ወንበር፣ የአስፋልት ማርኪንግ የተለያዬ ቀለም ማቅረብና በማሽን መቀባት፣ አልሙኒየም ማቅረብና መገጣጠም፣ የተፈጨ ጠጠር፣ የግንብ ድንጋይ እና አሸዋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች ህጋዊና የታደሠ የንግድ ወይም የስራ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
  3. የግዥ መጠን ከብር 700,000 በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. የሚገዙ የህንጻ መሳሪያ፣ የኤሌክትሪክ እቃ፣ የእግረኛ መንገድ የመብራት ፖል፣ የሳኒተሪ እቃ፣ ደስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ፣ ጠረንዸዛ፣ ወንበር፣ የአስፋልት ማርኪንግ የተለያዬ ቀለም ማቅረብና በማሸን መቀባት፣ አልሙኒየም ማቅረብና መገጣጠም፣ የተፈጨ ጠጠር፣ የግንብ ድንጋይ እና አሸዋ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሠነዱ ማገኘት ይቻላል።
  6. የህንጻ መሳሪያ ፣ የኤሌክትሪክ እቃ ፣ የእግረኛ መንገድ የመብራት ፖል ፣ የሳኒተሪ እቃ ፣ ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር ፣ ፕሪንተር ፣ ላፕቶፕ ፣ ጠረጴዛ ፣ ወንበር ፣ የአስፋልት ማርኪንግ የተለያዬ ቀለም ማቅረብና በማሸን መቀባት ፣ አልሙኒየም ማቅረብና መገጣጠም ፣ የተፈጨ ጠጠር ፣ የግንብ ድንጋይ እና አሸዋ ብር ወይም እቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% ከነቫቱ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
  7. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ግዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ 30 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል።
  8. የውጭ ሀገር ገንዘብ ምንዛሬ ተመን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኩል ለውጥ ከተደረገ በጨረታ ሰነድ ላይ የተሞላው ዋጋ የማይቀየር ወይም የዋጋ ማሻሻያ ተቋራጩ የማያደርግ መሆኑን
  9. በሀገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ቢጨምር ምንም አይነት የዋጋ ማስተካከያ ወይም የዋጋ ጭማሪ ሳያደርግ በጨረታ ሰነዱ ላይ በሞላው ዋጋ ብቻ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ ያቀርባል።
  10.  ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ ማለትም ለህንጻ መሳሪያ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/፣ ለኤሌክትሪክ እቃ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/፣ የእግረኛ መንገድ የመብራት ፖል የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ፣ ለሳኒተር እቃ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/፣ ዴስከ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ፣ ጠረጴዛ፣ ወንበር የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/፣ ለአስፋልት ማርኪንግ የተለያዬ ቀለም ማቅረብና በማሽን መቀባት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ለአልሙኒየም ማቅረብና መገጣጠም የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ የተፈጨ ጠጠር ፣ የግንብ ድንጋይ እና አሸዋ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል እድገት ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ መ/ቤት ማግኘት ይቻላል።
  11.  ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሣቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ እድገት ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሠዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሁሉም ጨረታዎች ለተከታታይ 16 ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሸጎ በ16ኛው ቀን 4፡30 ይከፈታል።
  12.  ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ እሰከ 16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰአት ድረስ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ በዚሁ ሰአት ይታሸጋል፡፡ የጨረታ ሳጥን ከታሸገ እና ጨረታ መከፈት ከጀመረ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ሲፒኦ ተቀባይነት የሌለውና ተጫራቹን ከጨረታ ውድድር ውጭ መ/ቤቱ የሚያደርግ መሆኑን እንገልጻለን።
  13.  ማንኛውም ተጫራቾች ያቀረበው የጨረታ ሰነድ ፖስታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ሲፒኦ የሌለው ከሆነ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሞላው ዋጋ የማይነበብና ተጫራቹም ከጨረታ ውድድር ውጭ የሚሆን መሆኑን እናሳውቃለን።
  14.  ማንኛውም ተጫራቾች ዋጋ መሙላት የሚችለው መ/ቤቱ ባቀረበለት የዋጋ መሙያ ሰነድ ብቻ ሲሆን በሌላ ወይም በራሱ የዋጋ መሙያ ሞልቶ ቢያቀርብ ተጫራች መ/ቤቱ ከጨረታ ውድድር ውጭ የሚደርግ እና በሁለት ዋጋ መሙያ ሞልቶ ያቀረበውን ተጫራች መ/ቤቱ በህግ የሚጠይቅ መሆኑን እናሳውቃለን።
  15.  ጨረታው ለሁሉም እቃዎች የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእድገት ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ መ/ቤት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ካልተገኙ ተቋራጩ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16.  አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ደሴ ከተማ እድገት ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ መ/ቤት ድረስ በራሱ ማጓጓዥ፣ የማስጫኛ እና ማውረጃ ወጭን ሸፍኖ ማቅረብ ይኖርበታል።
  17.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  18.  አሸናፊው ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ለውል ማስከበሪያ የሚሆን 10% የሚያስይዙ መሆኑን።
  19.  በጨረታ ለመሣተፍ የሚፈልጉና ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልከ ቁጥር 09 14 60 51 86/ 09 20 79 43 47 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

አድራሻ፡- ደሴ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ህንጻ 3ኛ ፎቅ

 

እድገት ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ

 

Save Tender