Tender Detail

Tender Details

  • Company Sidama National Regional State Road Development &Transport Bureau (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462121455
  • Website
  • Deadline06 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-06 00:00:00
  • Categories Vehicle (Garage Service)

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውል ዓመታዊ የተሽከርካሪ ጥገና ጋራዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

Sidama National Regional State Road Development &Transport Bureau (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ)


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 01

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውል ዓመታዊ የተሽከርካሪ ጥገና ጋራዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር መስፈርት መሠረት ለመሣተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የአቅርቦት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

  1. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው።
  2. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፣ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) በCPO ወይም ህጋዊ ባንክ ጋራንቲ (Unconditional Bank Guarantee) 190 ቀን ፀንቶ የሚቆይ በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ጨረታውን በሚወዳደሩበት ጊዜ በሁለት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ላይ ብቻ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ በቴክኒካል ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው ለ3 ወራት (90 ቀናት) ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
  7. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) ከፍሎ ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 104 በአካል ቀርበው መግዛት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች በመ/ቤቱ በተዘጋጀው ዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ላይ ብቻ የእጅ ዋጋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
  9. ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0462121455/ 0462122050

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ

 

Save Tender