Tender Detail

Tender Details

  • Company Wolaitta Development Association (የወላይታ ልማት ማህበር)
  • Address አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰሜን ሆቴል ፊት ለፊት ዳትስን ሰፈር ወደ ግራ በሚያስገባው አስፋልት 100 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0461801191
  • Websitehttps://wolaittada.org.et/
  • Deadline10 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-10 00:00:00
  • Categories Consultancy Service , Research Consultant

ወላይታ ልማት ማህበር አጠቃላይ የማህበሩን መዋቅራዊ አደረጃጀትን በሕጋዊ አማካሪ ለማስጠናት ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቶ አወዳድሮ አሽናፊውን በውል ለማሠራት ይፈልጋል።

Wolaitta Development Association (የወላይታ ልማት ማህበር)


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ወልማ 001/2025 እ.ኤ.አ

 

ወላይታ ልማት ማህበር አጠቃላይ የማህበሩን መዋቅራዊ አደረጃጀትን በሕጋዊ አማካሪ ለማስጠናት ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቶ አወዳድሮ አሽናፊውን በውል ለማሠራት ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው ለመሣተፍ (ለመወዳደር) የሚፈልጉ አማካሪ ድርጅቶች አሟልተው መቅረብ ያለባቸው መስፈርቶችና ግደታዎች፤

  1. ከሚመለከተው ሕጋዊ አካል ለ2017 በጀት ዓመት ታድሶ የተሰጠ የንግድ ሥራ /የሙያ ፈቃድ/፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ም/ም/ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ም/ም/ወረቀት፣ እና የንግድ (የሙያ) ም/ም/ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ም/ም/ወረቀት ማቅረብ፣
  2. ተጫራቾች በሥራ ላይ የሚያሣትፏቸውን ባለሙያዎች ብዛት፣ የትም/ደረጃ፣ የሥራ ልምድ ከእያንዳንዱ ባለሙያ ጋር የተፈፀመውን ቅጥር ውል ኮፒ ወዘተ ማቅረብ፣
  3. ተጫራቾች ስለመልካም ሥራ አፈፃፀማቸው ከአሁን በፊት መዋቅር ጥናት ካደረጉባቸው መ/ቤቶች (ድርጅቶች/ የተሰጣቸውን የድጋፍ ምስክር ወረቀት ማቅረብ፣
  4. ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋው 2% (ሁለት ፐርሰንት) በባንከ የተመሠከረለት ሲፒኦ ከጨረታ ዋጋ ማቅረብያ ሰነድ ጋር አያይዞ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ፣
  5. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ በተከታታይ ባሉት አሥራ አምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በማህበሩ ሥራ ሰዓት ከወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት እና በአ/አበባ ከተማ ዳትሰን ሰፊር ከሚገኘው ከወላይታ ልማት ማህበር አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የቴክኒክና ፋይናንሻል የመወዳደሪያ ሀሳቦች ዋናውንና ፎቶኮፒውን ለየብቻ ስምና አድረሻውን በፖስታ (በኤንቨሎፕ) ላይ በትክክል በመጻፍና ማህተም በማድረግ አሽገው በወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 15ኛው በማህበሩ ሥራ ቀን እስከ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሣጥኑ በ15ኛው በማህበሩ ሥራ ቀን ልክ በ9፡20 ሰዓት ታሽጎ (ተዘግቶ) ፈቃደኛ የሆኑ ተጫራቾች ሕጋዊ ተወካዮችና ታዛቢዎች በተገኙበት ልክ ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት በወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል በይፋ ይከፈታል። 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በሕጋዊ በዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው ሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።
  7. በጨረታው አሸናፊ የሆነው አማካሪ ድርጅት የጠቅላላ ዋጋው 10% (አሥር ፐርሰንት) የውል ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በኢት/ያ ንግድ ባንክ በተመሠከረ ሲፒኦ በማቅረብ ውል መፈረም አለበት። ለማስያዝ ፈቃደኛ ካልሆነ ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለማህበሩ ውርስ ይደረጋል።
  8. አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ እና አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ አለመቅረብ የጨረታ ዋስትናውን ያስቀጣል።
  9. አንድ ተጫራች የሚያሠራው ሲፒኦ በሕጋዊ ባለመብት ወይም ድርጅት ስም መሆን አለበት።
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም ግልጽ ሆኖ ካልታየ ተቀባይነት አይኖረውም ወይም ከውድድር ውጭ ሊያስደርግ ይችላል።
  11. ልማት ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ

ስልክ ቁጥር 0461801191: 0913177985: 0916833499 መጠቀም ይችላሉ።

 

የወላይታ ልማት ማህበር

 

Save Tender