በማእከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጉብሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በሥሩ ላሉት ድልድይ ስራ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የአርማታ ብረቶችን ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በማእከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የጉብሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጉብሬ ዲስትሪክት 002/2017
በማእከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጉብሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በሥሩ ላሉት ድልድይ ስራ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የአርማታ ብረቶችን ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጋቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ስራ ወይንም የአገልግሎት ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና ኦርጅናል እና አንድ ፎቶ ኮፒ በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውን በተለየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ከዲስትሪክቱ ጽ/ቤት የቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፤
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን — ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፣ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይት የለውም።
- ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0113220325 /0113220327 /0113220328
በማእከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የጉብሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
