ሪፕል ኢፈክት ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት ከስታር ባክስ ፋዉንዴሽ (Starbucks Foundation) ጋር በመተባበር በሲዳማ ክልል በቤንሳ ወረዳ የሚገኙ አነስተኛ የመሬት ይዞታ ያላቸው ቡና አብቃይ ሴት አርሶ አደሮችን አቅም ማጎልበት (Resilent and Empowerd Women and Grits in Coffee Growing Communities in Bensa District) ለተባለው ፕሮጀክት ለተጠቃሚ አርሶ አደሮች የሚሆን የእንስሳት መኖ ሳር ግንጣይና ዘር ህጋዊ ፈቃድ ካላቸውና በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል።
ሪፕል ኢፈክት ኢትዮጵያ
የእንስሳት መኖ ሳር ግንጣይና የዘር ግዢ ጨረታ
ሪፕል ኢፈክት ኢትዮጵያ (በቀድሞ ስሙ ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ) እ ኤ አ ከ 2006 ጀምሮ በኢትዮጵያ በዘላቂ ግብርና፤ እንስሳት አያያዝ፤ ተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ ፤ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ቅነሳ እና መሰል የልማት ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው።
በአሁን ሰዓት ድርጅቱ ከስታር ባክስ ፋዉንዴሽ (Starbucks Foundation) ጋር በመተባበር በሲዳማ ክልል በቤንሳ ወረዳ የሚገኙ አነስተኛ የመሬት ይዞታ ያላቸው ቡና አብቃይ ሴት አርሶ አደሮችን አቅም ማጎልበት (Resilent and Empowerd Women and Grits in Coffee Growing Communities in Bensa District) ለተባለው ፕሮጀክት ለተጠቃሚ አርሶ አደሮች የሚሆን የእንስሳት መኖ ሳር ግንጣይና ዘር ህጋዊ ፈቃድ ካላቸውና በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በዘርፉ የተሰማራችሁ ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዶቻቸሁን ከታች በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ በማስገባት እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
- የጨረታ መደብ /Lot / 1፡- የእንስሳት መኖ ሳር ግንጣይና ዘር
|
ተ.ቁ |
የእቃው ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
ምርመራ |
|
1 |
የዝሆን ሳር /Elephant/ Napier grass |
ቁርጥራጭ |
133,000 |
ከበሽታ ነፃ፤ ቢያንስ ሶስት እንቡጦች ያሉት |
|
2 |
የደሾ ሳር / Desho grass |
ግንጣይ |
133,000 |
ከበሽታ ነፃ የሆነ፤ |
|
3 |
አልፋልፋ ዘር / Alfalfa |
ኪሎ ግራም |
117 |
የጥራት መጠኑ ከ95% በላይ፤ የብቅለት መጠኑ ደግሞ፤ ከ85% መሆን አለበት |
|
4 |
የእንስሳት ጓያ ዘር / Vetch seed |
ኪሎ ግራም |
167 |
የጥራት መጠኑ ከ95% በላይ፤ የብቅለት መጠኑ ደግሞ፤ ከ85% የሆነ |
|
5 |
ሲናር ዘር / oat seed |
ኪሎ ግራም |
500 |
የጥራት መጠኑ ከ95% በላይ፤ የብቅለት መጠኑ ደግሞ፤ ከ85% የሆነ |
|
6 |
ደዝሞዲየም ዘር / Desmodium seed |
ኪሎ ግራም |
33 |
ባለ አረንጓዴ ቅጠል፤ የጥራት መጠኑ ከ95 በመቶ በላይ፤ የብቅለት መጠኑ ከ85 በመቶ በላይ የሆነ |
- ተጫራቾች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነትና ለ2016 ዓም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል።
- ተጫራቾች መወዳደር ለሚፈልጉት የጨረታ መደብ በተለያየ ፖስታ በስም ማሸግና ማህተም ማድረግ እንዲሁም የጨረታ መደቡን ቁጥር በመጻፍ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- አንድ ድርጅት በአንድ ወይም ከአንድ በላይ የጨረታ መደቦች መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅርቢያቸው ላይ ዋጋው ጸንቶ የሚቆይበትን ጊዜ እና ቫት ማካተት አለማካተቱን መገለጽ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ማስገቢያ ፖስታው ላይ የጨረታው መደብና ቁጥር መገለጽ ይኖርበታል።
- ተጨራቾች በተጠየቁ ጊዜ ዋጋ ያስገቡለትን ቁሳቁስ ናሙና ለማሳየት ወይም ለማቅረብ ፈቃደኛ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ሪፕል ኢፌክት ኢትዮጵያ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻችሁን ከታች በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ ማስገባት ይኖርባችኋል፡
- የጨረታ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ስምንት የስራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ አድራሻ፡ ሪፕል ኢፈክት ኢንተርናሽናል ካሳንችስ ወረዳ 08 ከ ኢሊሊ ሆቴል ቀጥሎ SA ሕንጻ (ህብረት ባንክ ያለበት) ፤ 7ተኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር (+251)-11-6-47-72-33/34 1 አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ ወይም ሪፕል ኢፌክት ኢንተርናሽናል በንሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በንሳ፤ ዳዬ ከተማ
ስልክ: +251 913544299/909887698
