Tender Detail

Tender Details

  • Company ሆሳዕና ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት
  • Address ሆሳዕና : ኢትዮጵያ, Phone: +251465552345
  • Website
  • Deadline04 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-04 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Cloth And Shoes

የሆሳዕና ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የደንብ ልብሶች ከህጋዊ ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሆሳዕና ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሆሳዕና ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የደንብ ልብሶች ከህጋዊ ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት - 1. የወንዶች እና የሴቶች ቆዳ ጫማ፣

ሎት- 2. ፓሊስተር እና ቦብለን ብትን ጨርቅ ፣ ሸሚዝ እና የዝናብ ዣንጥላ፣

  1. ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው የሚገልጸውን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ ቀናት ሆ/ከ/ው/አገ/ድርጅት ቢሮ ቁ- 9 ቀርበው በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና በሚመለከተው መ/ቤት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. የጨረታ ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናል ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ከሁለት ኮፒ ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ጋር በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁ. 9 በመምጣት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  6. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆ/ከ/ው/አ/ድርጅት ቢሮ ቁጥር 9 ውስጥ ይከፈታል። ሆኖም ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  7. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ዋስትና ተመላሽ የሚሆነው አሸናፊው ድርጅት በጽሁፍ ከተገለጸ በኃላ ይሆናል።
  8. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለጸ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ ገንዘብ ማስያዝ ሆ/ከ/ው/አገ/ድርጅት ውል መፈራረም አለበት።
  9. የእቃዎች ርክክብ በሆ/ከ/ው/አ/ድርጅት ግምጃ ቤት ይሆናል።
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- +251-4-65-55-23-45 ሞባይል 09-12-71-81-04

 

ሆሳዕና ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት

 

Save Tender