በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለገ/ጉ/ወ/ወረዳ ከተማ ልማት ጽ/ቤት የደረቅ ቆሻሻ ጉድጓድ ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር GGWW/30/2017
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለገ/ጉ/ወ/ወረዳ ከተማ ልማት ጽ/ቤት የደረቅ ቆሻሻ ጉድጓድ ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች:-
- CPO ለደረቅ ቆሻሻ ጉድጓድ 25000 /ሀያ አምስት ሺ/ ብር
- የዘመኑ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/BC ደረጃ 8 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቋራጮች
- በጨረታው ለመወዳዳር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ የድርጀቱ ባለቤት መሆን አለባቸው እንዲሁም በውክልና ሰነዱን መውሰድና መወዳደር አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰአት ድረስ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀልአምባ ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሀ/ ለቴከኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማደረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ / ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ቴክኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት መሀል አምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነድ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መስሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ:-
- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች ተጫርተው ካሸነፉ በኋላ አገልግሎታቸው ጥራት ያለውና ቀልጣፋ ካልሆነ የውል ጊዜን የምናቋርጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
- በወረዳው ውስጥ ሁለት እና ከዛ በላይ ፕሮጀክት የያዘ አካል መወዳደር አይችልም፡፡
- ተወዳዳሪዎች ከአሸነፉ በኋላ ቅደመ ክፍያ ሳይጠይቁ ስራው መስራት የሚችሉ መሆን ፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ስልክ ቁጥር 0113360631/146 ይደውሉ
ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
መሀል አምባ
