የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የስፖርት ምክር ቤት በተያዘለት በጀት የተለያዩ የስፖርት ግብዓት ግዥዎችን በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር ቤት
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የስፖርት ምክር ቤት በተያዘለት በጀት የተለያዩ የስፖርት ግብዓት ግዥዎችን በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች በተገለፀው 2 ሎት መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
ሎት 1 የስፖርት ትጥቅ
ሎት 2 ለክፍለ ከተማው የጂም ቤት ግብዓት
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ፤ ቲን ሰርተፍኬት የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ የታክስ ክሊራንስ እንዲሁም ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች ዋናውንና ኮፒውን በማቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በኤንቨሎፕ ታሽጎ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ እንዲሁም ፋይናንሺያል ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል የመንግስት ግዥ ቡድን ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው እስከ 11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ሰነዱ ተመላሽ ተደርጎ በዚህ ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ላይ በተገለጹት ሎቶች በሙሉ ወይም መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን አድራሻቸውንና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ በመፈረም ማቅረብና ማረጋገጥ አለባቸወ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1:- 10,000 (አስር ሺህ ብር) ለሎት 2 40,000 (አርባ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከሆኑ ከአዳራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል የመንግስት ግዥ ቡድን ስም ተሰርቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- በስፖርት ትጥቅ ጨረታ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- በሎት 2 ለሚወዳደሩ ተጫራቾች በዚሁ ዘርፍ ሌላ ቦታ ላይ የሰሩበት 3 የመልካም ስራ አፈፃፀም ደብዳቤ ከህጋዊ ተቋም ማቅረብ እንዲሁም በቂ ስቶክ መኖሩን የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆኖ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ኮ/ቀ/ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 የሚገኘው የክፍለ ከተማው ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 ስልክ ቁጥር 0118347732
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር ቤት
