የጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የተለያዩ የሚጠገኑ ላፕቶፕ፣ እስካነር፣ የፎቶ ኮፒ ማሸን፣የኤሌክትሪካል እና የመካኒካል እቃዎች፣ ላፕቶፕ፣ ፕሪንተር፣ ዴስክ ቶፕ የኮምፒውተር እቃዎች፤ ተሽከርካሪ (62 ሰው የመጫን አቅም ያለው የሰራተኛ ባስ) ፤ የመለዋወጫ እቃዎች እና የሞተር ዘይቶች አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን ስለሚፈልግ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
የጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 003/2017
የጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የተለያዩ የሚጠገኑ ላፕቶፕ፣ እስካነር፣ የፎቶ ኮፒ ማሸን፣የኤሌክትሪካል እና የመካኒካል እቃዎች፣ ላፕቶፕ፣ ፕሪንተር፣ ዴስክ ቶፕ የኮምፒውተር እቃዎች፤ ተሽከርካሪ (62 ሰው የመጫን አቅም ያለው የሰራተኛ ባስ) ፤ የመለዋወጫ እቃዎች እና የሞተር ዘይቶች አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን ስለሚፈልግ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳድሩበትን ከላይ ለተገልጹት ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 1% በባንከ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የታድሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት እና የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመከፈል መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ (ሃና ማሪያም አፍሪካ ስድስት ፊለፊት የቀድሞ ሪቬራ ሆቴል) ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው የተለያዩ እቃዎችን ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- የጨረታው አሸናፊ ውል ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ ዕቃውን በራሱ ትራንስፖርት በሰጠው ናሙና መሰረት በጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ11ኛ (አስራ አንደኛው) ቀን 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4:30 ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት በመክፈል መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ይከፈታል።
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መከፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም። ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆን በከፊል የመሰረዝ ሙበቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በአንድ ተመሳሳይ ዕቃ ላይ ሁለት የተለያየ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
ስልክ ቁጥር 011 433 88 09/09 11 86 99 62/09 18 11 93 25
የጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
