የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት በተፈቀደለት በጀት የተማሪዎች ምግብ ግባአት ግዥ በብሄራዊ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።
Debre Markos University (ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ደ/ማ/ዩብ/ግ/ጨ/26/2017
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት በተፈቀደለት በጀት የተማሪዎች ምግብ ግባአት ግዥ በብሄራዊ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ከዚህ በታች ማለትም፤
- በዘመነ እና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት እና የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- አሸናፊው ድርጅት ለሁለት ዓመት ውል በመያዝ
- ሎት 1 የምግብ ዘይት
- ሎት 2 የማገዶ እንጨት
- ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ሎት1 ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- ሎት 2 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሰርቶ ማቅረብ የሚችል ወይም በጥቃቅን የተደራጁ ከአደራጃቸው የመንግስት መ/ቤት ከላይ የተገለጸውን የገንዘብ መጠን የሚገልጽ የዋስትና ደብዳቤ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም በማሰራት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 / ሶስት መቶ ብር / ለእያንዳንዱ ሎት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዪኒቨርስቲው ስም በተከፈተው የሂሳብ ቁጥር 1000017980517 በመክፈል ደረሰኝ በማቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ፋይናሽያል አርጅናል እና ቴክኒካል ሰነዶችን ኮፒ ዶክመንት በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለፀለት ከ7 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ከ8ኛ ቀን ጀምሮ በተከታታይ በ8 የስራ ቀናት ውስጥ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት፣
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከተከታታይ 15 ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡59 ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ላይ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ውስጥ ይከፈታል ነገር ግን የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀኑ የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል ፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታ ጨምሮ በእለቱ ይከፈታል፡፡
- የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 058 771 66 91 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡ ፡
ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
