በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር የሚገኙ ቁርጥራጭ ብረቶችንና ተረፈ ምርቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት
ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2017
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር የሚገኙ ቁርጥራጭ ብረቶችንና ተረፈ ምርቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታ የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የንብረቱን አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ከላይ የተጠቀሱትን እቃዎች ዝርዝር የሚያሳይ የግዥ መመሪያ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 20 መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 5000 (አምስት ሺ) አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል ስም የተዘጋጀ CPO ከመወዳደሪያ ሰነዶቻችሁ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጋዜጣው ላይ በወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችሁ በተገኙበት የተወከሉበትን የውል ማስረጃ እና መታወቂያ በመያዝ በአ/ክ/ከ/ወ/7 ፋይናንስ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶች በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ቀበና ወጣት ማእከል ግቢ ውስጥ በአካል በመምጣት ማየት ይቻላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጠቅላላ ዋጋው መሰረት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በፖስታው ላይ ማነታቸውን የሚገልጽ ስም ከነአያታቸው፤ የመታወቂያ ኮፒ ስልክ ቁጥር መጻፍ አለባቸው፡፡
- መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው ፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር 0111222848 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ ሳንፎርድ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት
አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት
