አልሺማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኝ የ2017 ሞዴል ሊፋን X60 ቻንሲ ቁጥር LCN64ED50M0097133፤ የሞተር ቁጥር LFB479Q*170300359* ተሽከርካሪን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
አልሺማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
የተሽከርካሪ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/የም/አም/ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሽያጭ /0007/2025
አልሺማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኝ የ2017 ሞዴል ሊፋን X60 ቻንሲ ቁጥር LCN64ED50M0097133፤ የሞተር ቁጥር LFB479Q*170300359* ተሽከርካሪን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያመሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት መጫረት ይችላሉ።
- ማንኛውም የመጫረት ፍላጎት ያለው በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ ለተጫረቱበት ተሽከርካሪ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ከሲፒኦ ውጪ የሚያቀርቡ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ተሽከርካሪው አ/አ ቦሌ መድሀኒያለም ሂድሞና ህንፃ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታ በአካል በመቅረብ ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ አሸናፊው ተለይቶ ከታወቀ በኋላ የሚመለስ ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ ለተሽከርካሪው የሚከፈሉ ማንኛውንም የመንግስት ክፍያዎችን ሁሉ ይሸፍናል።
- ማንኛውም ተጫራች ሌሎች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- የጨረታው አሸናፊ መሆኑ የተገለፀለት ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው 10% (አስር በመቶ) እንደውል ማስከበሪያ ይቆጠራል። የጨረታው አሸናፊ የገባውን ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ዋስትና እንደ ውል ማስከበሪያ ተቆጥሮ የተያዘውን ገንዘብ አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ወደ ራሱ ካዝና ገቢ ያደርጋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ መምሪያ አዳማ ወይንም አዲስ አበባ ከሚገኘው ቢሮ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ለጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተሞላ ወይንም በሌላ ወረቀት ላይ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው ባቀረበው የመግዣ ዋጋ መሠረት ብቻ ነው።
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በተገለጸ በ7 ቀናት ውስጥ በአካል ቀርቦ ውል መፈፀም አለበት።
- የጨረታው አሸናፊ ውል እንዲፈፅም በተገለፀለት በ7 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ባይፈፅም ድርጅቱ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘውን ዋስትና ወደ ራሱ ካዝና ገቢ ያደርጋል።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-639-2511
አልሺማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
