Tender Detail

Tender Details

  • Deadline31 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-31 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ለአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለመልሶ ማቋቋሚያ አገልግሎት የሚውሉ ከዞን ማዕከላት ወደ የተለያዩ ወረዳዎች ምግብና ምግብ ነክ-ያልሆኑ ቁሳቁሶች ማጓጓዣ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ አግባብ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 337/17

 

የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ለአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለመልሶ ማቋቋሚያ አገልግሎት የሚውሉ ከዞን ማዕከላት ወደ የተለያዩ ወረዳዎች ምግብና ምግብ ነክ-ያልሆኑ ቁሳቁሶች ማጓጓዣ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ አግባብ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በንግድ ሥራ ዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመከፈላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የአቅራቢነት ምዝገባ እና የቫት ተመዝጋቢነትን ማስረጃ ያላቸው ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀን የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋቸው 2% ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ለጨረታው የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ/በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል በዲላ ከተማ ከሚገኘው ግብርና ቢሮ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡40 ሰዓት ተጫራቾች/ ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  • 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ላይ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል ፡፡
  • ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20 ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡
  • ሁለት ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋቸው እኩል በሚሆንበት ወቅት በዕጣ የሚለይ ይሆናል ፡፡
  • መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 131 0134

ማሳሰቢያ፡- የምግብና ምግብ ነከ-ያልሆኑ ቁሳቁሶች ማጓጓዣ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ጫኝና አውራጅን ጨምሮ ማቅረብ ይኖርበታል።

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ

 

Save Tender