የቦዲቲ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ህጋዊ አማካሪ ድርጅት አወዳድሮ የድርጅቱን መዋቅርና ጥቅማጥቅም ጥናት ፣ የሰው ሀይል ማንዋል፣ የግዥ መመሪያ፣ የፋይናንስ መመሪያ፣ የንብረት አስተዳደር መመሪያ ፣ የስራ አመራር መተዳደሪያ ደንብ ፣ የቦርድ መተዳደሪያ ደንብ ማንዋል እና የቢዝነስ ፕላን ማስጠናት አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቦዲት ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቦዲት ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ገቢውን ከፍ ለማድረግ የተቋቋመበትን ዓለማ ማሳካት እንዲችል በስሩ የቦዲቲ ከተማ የውሃና ውሃ ነክ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት አቋቁሟል፡፡
የቦዲቲ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ህጋዊ አማካሪ ድርጅት አወዳድሮ የድርጅቱን መዋቅርና ጥቅማጥቅም ጥናት ፣ የሰው ሀይል ማንዋል፣ የግዥ መመሪያ፣ የፋይናንስ መመሪያ፣ የንብረት አስተዳደር መመሪያ ፣ የስራ አመራር መተዳደሪያ ደንብ ፣ የቦርድ መተዳደሪያ ደንብ ማንዋል እና የቢዝነስ ፕላን ማስጠናት አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላል፡፡
- የስራ አመራር ማማከር የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያለው፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፤ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው፤
- በስራ አመራር ማማከር ፈቃዱ ከ4 ዓመት በላይ ሰርቶ የሚያውቅ መሆን አለበት፡፡
- ቀጥታ አግባብ ያለው ትምህርት ዝግጅት በሚመለከት በመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ በቢዝነስ፣ በማነጅመንት፣ በአካውንትንግና ፋይናንስ በተጨማሪ አግባብ ያለው ስልጠናዎችን የወሰደ፤
- ይህን ስራ በውሃ አገልግሎት ሁለትና በላይ የሰራ ፣ በሌሎች ከ4 ተቋማት በላይ የሰራ ፤ በተመሳሳይ ልምድ፤
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በ(CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው ለእያንዳንዱ ሥራ ያቀረበው የአንዱ ስራ ዋጋ ዝቅተኛ ዋጋ መሠረት ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች የጨረታ ውል ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ 10% ከታወቀ ባንክ ማስያዝ ይኖርበታል።
- አሸናፊ ተጫራች ስራውን አጠናቆ ለውሃ ቦርድ በማቅረብ የማስተቸት ግዴታ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀን በአየር ላይ ከቆየ በኋላ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በጽ/ቤታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ ከቢሮ ቁጥር 03 በመግዛት መጫረት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት በተራ ቁጥር 9 በተገለጸው የስራ ቀን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጂናሉንና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ቢሮ ቁጥር 03 ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ማስገንዘቢያ፡-
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከአስፈለገ በስልክ ቁጥር +251913698323 ወይም +251921832296 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቦዲት ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
