የራያ ዋከና ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ሃላፊነቱ የተወሰነ ያገለገሉ ሁለት (2) ጃንደር ኮምፓይነሮችን በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የራያ ዋከና ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ሃላፊነቱ የተወሰነ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የራያ ዋከና ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ሃላፊነቱ የተወሰነ ያገለገሉ ሁለት (2) ጃንደር ኮምፓይነሮችን በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እያሳሰብን፡-
የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ኮምፓይነሮቹ በሚገኙበት አድራሻ በአካል በመገኘት መመልከት የሚችል ይሆናል።
- ተጫራቾች በሚገዙት ኮምፓይነር ከጠቅላላ ዋጋ 5 በመቶ (5%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ለ 30 ቀናት የሚቆይ ዋስትና አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ መግዣ የሚውል 500 የማይመለስ ብር (አምስት መቶ ብር) ለዩንየኑ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለ አሸናፊዎች ከሚከፈሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራቾች የተሳሳተ መረጃ ማቅረባቸው ከተረጋገጠ ዩንየኑ ከውድድሩ ማሰናበት ይችላሉ።
- ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን አንስተው በአምስት (5) ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን ከጨረሱ በኋላ ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
- የሰነድ ሽያጭ የሚቆይበት ቀን ከ8/9/17 እስከ 6/10/17 ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ6/10/2017 ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዛው እለት በ 4፡30 የዩንየኑ ቦርድ አባላት እና ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚገዙት ሰነድ ውስጥ ስም እና ሙሉ አድራሻ በግልፅ በማስቀመጥ ፊርማውንና ማህተሙን መምታት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ በሚቀርበው ሰነድ ውስጥ ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ሰነዱን ሞልተው ሲያስገቡ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖረው አድርገው መስራት አለባቸው / ስርዝ ድልዝ ካለው የተጫራቹ/ ተወካዩ ፊርያ ከፊት ለፊቱ መኖር አለበት። እንዲሁም ደግሞ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን እና ሰነዱን በ አንድ ፖስታ አሽገው በማህተም በማረጋገጥ አሽገው ማስገባት አለባቸው።
- ዩንየኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በ ሙሉ ወይም በ ከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው ላይ የሚሳተፍ ተጫራች አንድ ወይም ሁለት ኮምፓይነሮች ላይ መጫረት ይችላል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች የንብረት ስም ዝውውር በሚያደግበት ሰዓት ወጪውን በራሱ የሚሸፍን ይሆናል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ኮምፓይነሩን ሲረከብ ከነ ሙሉ እቃው ይሆናል፡፡
- የምዝገባ ሰዓት ጠዋት 2፡30-6፡30 ከ ሰዓት ከ 7፡30-11፡00 የስራ ሰዓት ይሆናል።
አድራሻ :- ኦሮሚያ ክልል ፣ ም/ዕ አርሲ ዞን ፣ ዶዶላ ከተማ 02 ቀበሌ ፣ ፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ ጎን ይገኛል ።
የራያ ዋከና ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ሃላፊነቱ የተወሰነ
