ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ምስራቅ ሪጅን ስር የሚገኙ ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታብረቶችን ባሉበት ሁኔታ ለብረታብረት ፋብሪካዎች ቅድሚያ በመስጠት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም
ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን
ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ
የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 07/2017
የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት ቀን ግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም፣
ጨረታው የሚዘጋበት ቀን ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም፣
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ግንቦት 29 ቀን 2017 ዓ.ም፣
ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ምስራቅ ሪጅን ስር የሚገኙ ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታብረቶችን ባሉበት ሁኔታ ለብረታብረት ፋብሪካዎች ቅድሚያ በመስጠት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ደሴ/ፒያሳ በሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል እና በመግዛት መወዳደር የምትችሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትፈልጉ ተጫራቾች ደሴ/መላኩ አካባቢ በሚገኘው ዋናው ዕቃ ግ/ቤት ቢሮ በመገኘት መጠየቅ ይቻላል፣ እንዲሁም ንብረቶቹን መመልከት ለሚፈልጉ ደሴ ካራጉቱ በሚገኘው ዕቃ ግምጃ ቤት የታደሰ መታወቂያችሁን እና የጨረታ ሰነዱን የገዛችሁበትን ደረሰኝ በመያዝ መጎብኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደሴ/ፒያሳ በሚገኘው ዋናው ጽ/ቤት ግንቦት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የሰ/ምስ/ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም
