በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለ2017 ለሥራ የሚገለገልበትን Lot 1 A4 Computer Paper በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት
ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለ2017 ለሥራ የሚገለገልበትን Lot 1 A4 Computer Paper በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (VAT) ያላቸው፣
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
- ተጫራች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰባት (07) ተከታታይ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በመ/ቤቱ ቀርቦ መግዛት ይችላል።
- ለጨረታው ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት የዕቃ ዋጋ ብር 1% በተረጋገጠ ባንክ (cpo) በድርጅቱ ስም አሰርቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የእቃውን ስፔሲፊኬሽን ከድርጅቱ በቀረበው መሠረት በግልፅ በመፃፍና ዕቃው ላይም በግልፅ መታየት ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን አሟልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቀርቦ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ በ7 ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ተከታታይ ቀናት ጠብቆ በ7ኛው ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በዛው ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ በእለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
- ድርጅቱ ከሰጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ ማስተካከያ ማድረግ እና መሰረዝ (Material Devation) አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች በድርጅቱ ዋጋ ማቅረቢያ የድርጅቱ ኦርጅናል ማህተም (የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት የሚል ማህተም) ባረፈበት ላይ ብቻ የዕቃ ዋጋዎችን ሞልቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ከድርጅቱ ዋጋ ማቅረቢያ ውጪ የሚመጡ ሰነዶች ዋጋ የላቸውም፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ድርጅታችን ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክተር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 437-16-83 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት
