Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-2-20-20-77
  • Website
  • Deadline30 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-30 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing

ሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የፈርኒቸር ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡

የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ 03/2017

 

ሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የፈርኒቸር ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡

በዚሁ መሠረት -

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው ፤ የዘመኑን ግብር የገበረ
  2. የቫት /VAT/ ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ያለው
  3. የግብር ከፋይ /TIN/ መለያ ቁጥር ያለው
  4. የዕቃና የአገልግሎት አቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1- 4 የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ ሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 30 በመክፈል ሠነዱን መውሰድ ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ CPO 12,000 /እና Bid Bond የ90 ቀን በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስም በማሰራት ማቅረብ የሚችል፡፡
  8. ተጫራቾች የፋይናሻል ዶክመንት ኦርጂናል 1 እና 2 ኮፒ በተለያየ በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጂናል1 እና ኮፒ 1 በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት ከ15 የስራ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች / ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል / የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊ ዕቃውን በራሱ ወጪ አጓጉዞ መጋዝን ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  11. የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በማስታወቂያ ይገለጻል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0462202077

 

የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት

 

Save Tender