የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ከሐምሌ 01/11/2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/10/2018 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ለሕግ ታራሚዎች የምግብ ጥሬ እህል፤ አጥንት የሌለው የበሬ ሥጋ ማጣፈጫዎችን (ልዩ ልዩ ሸቀጣሸቀጦችንና የማገዶ እንጨት በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ከሐምሌ 01/11/2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/10/2018 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ለሕግ ታራሚዎች የምግብ ጥሬ እህል፤ አጥንት የሌለው የበሬ ሥጋ ማጣፈጫዎችን (ልዩ ልዩ ሸቀጣሸቀጦችንና የማገዶ እንጨት በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ ሰርቴፍኬትና ቲን ነምበር / Tin Number/ ያለው የዘመኑን ንግድ ግብር አጠናቆ የከፈለ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 / ሃምሣ ሺህ ብር ብቻ / በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችልና ጨረታውን ያለፈ እያንዳንዱ ሰው ባለፈው ልክ የውል ማስከበሪያ ብር 150,000.00 / አንድ መቶ ሃምሣ ሺህ ብር ብቻ ጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝና በጨረታው ደንብ የተጠቀሱትን መስፈርቶችን ሁሉ ማሟላት የሚችል ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባለው 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00 / ሁለት መቶ / በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ቢሮ ቁጥር 08 ቀርቦ በመግዛት በሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የምግብ ጥሬ እህል ፤ ማጣፈጫና የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦችን በዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀው የምግብ ጥሬ እህል ፤ ማጣፈጫዎችንና ልዩ ልዩ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦችን ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በጋዜጣው ላይ በተጠቀሰው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 /ሶስት ሰዓት / ላይ ተጫራቾች / ሕጋዊ ወኪሎቻቸው/በተገኙበት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ በጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ውስጥ የሚከፈት መሆኑንም ጭምር እንገልጻለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
-
- ተጫራቾች በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የሁሉ ዕቃ ዓይነት ዋጋ መሙላትና ዋጋቸውን አባዝተው የማስቀመጥ ግዴታ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊ በጨረታ ያሸነፋቸውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ወደ ተቋሙ ማድረስ አለበት፡፡
- በተጨማሪ ናሙና የማቅረብ ግዴታ ያለባቸው መሆኑን እያሳወቅን ማረሚያ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0467760126 0467760125 በመደወል ማረጋገጥ ይቻላል::
የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም
