በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ ተሽከርካሪዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሀራጅ ጨረታ ቁጥር፡- 044/2017
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ ተሽከርካሪዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 044/2017 በ14/09/2017 ዓ.ም ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎችን ለመጫረት የሚፈልጉን
ተጫራቾች፤
- ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ዲጂታል/ ብሔራዊ መታወቂያ ያለው።
- ለጨረታ የቀረበው ተሽከርካሪ ሲሆን የሚገኘው ድሬዳዋ ሙዲአነኖ ግቢ በሚገኘው ተሽከርካሪ መጋዘን ውስጥ ነው።
- የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የሆነ ሰው በጨረታ መሳተፍ አይችልም፡፡
- በጨረታው ሰነድ ላይ በተገለጸው መስፈርት መሰረት ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ቀኑ 12፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሰነዱን በመግዛት እና ሪሲት በመውሰድ ተሽከርካሪው በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል።
- ተሽከርካሪውን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ድሬዳዋ ሙዲአነኖ የሚገኘው ግቢ ውስጥ ነው።
- ተጫራቾች ለተሽከርካሪው የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ተሽከርካረውን ለመግዛት ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ 5% በንግድ ባንክ የተረጋገጠ (CPO) በድሬዳዋ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
- የሐራጅ ጨረታው ለሚካሄደው በማስታወቂያ መሰረት በእለቱ ጠዋት በ2:00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ጨረታው ይጀምራል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመሳሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን ተሽከርካሪ አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድግ ተሽከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 11 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ተሽከርካረውን ያልተረከበ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
- የጉምሩክ ኮምሽን ድ/ዳ/ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት
