በኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በበጀት አመቱ የሚያስፈልጉ የSOUND SYSTEM ዕቃዎች ከነ installation በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ግዥ ለመፈፀም ብቃትና ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር CC-MOBO/NCB/12/2017/2025
በኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በበጀት አመቱ የሚያስፈልጉ የSOUND SYSTEM ዕቃዎች ከነ installation በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ግዥ ለመፈፀም ብቃትና ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው የሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግሥት በመንግሥት ግዥ አዋጅ በተገለጸው ብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓት መሠረት ይሆናል። በሎት 1 ላይ የተጠቀሰው እቃዎችን ግዥ ጨረታ የሚከናወነው ብቁ ከሆነ ተጫራች እና ከአቅርቦቱ ጋር አግባብነት ያላቸው ሆኖ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑ ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽ ታክስ ክሊራንስ የኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዌብሳይት ላይ የአቅራቢነት ዝርዝር (Supplier List) ፕሪንት አርጎ ማምጣት አለባቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ በአካል በመገኘት መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር በመቶ) C.P.O በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው አድራሻ ጨረታው ከወጣበት ግንቦት 06 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 20 ቀን 2017 ጠዋት 4:30 ላይ ይከፈታል። ዘግይተው የቀረቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
- ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች/አቅራቢዎች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ተጫራቹ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ በባንክ በተመሰከረለት 5% C.P.O ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርበታል።
- የጨረታው ሰነድ የሚገባበት አድራሻ የሞያሌ ጉምሩከ ቅ/ፅ/ቤት ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ቡድን ቢሮ።
- ዘግይቶ የመጣ ተጫራች ፖስታ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸው ማህተም እንዲሁም ስም፣ አድራሻ፣ ስልክ፣ኢሜይል አድራሻ ማድረግ አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች ተመሳሳይ ዋጋ ቢያቀርቡ ቃለ ጉባኤ በመያዝ በእጣ የምንለይ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ቅ/ፅ/ቤቱ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው።
የጨረታ ሰነድ መሸጫና ጨረታ መክፈቻ ቦታ የሞያሌ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን አስተባባሪ 2ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር:- 0913995723/0926423950/
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት
