Tender Detail

Tender Details


በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የብር ሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት በ2017 በጀት በ4ኛ ሩብ ዓመት በሎት 1 የተለያዩ የቀለብ ዓይነቶችን፣ በሎት 2 የተለያዩ የጽሕፈት ዕቃዎችን እንዲሁም በሎት 3 የተለያዩ የግንባታ እና የቧንቧ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የብር ሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የብር ሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት በ2017 በጀት በ4ኛ ሩብ ዓመት በሎት 1 የተለያዩ የቀለብ ዓይነቶችን ፣ በሎት 2 የተለያዩ የጽሕፈት ዕቃዎችን እንዲሁም በሎት 3 የተለያዩ የግንባታ እና የቧንቧ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተጫራች ማሟላት የሚገባቸው፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው፣
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  4. የግብር ከፋይ ምዝገባ (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል፤
  5. የዘመኑ ግብር የከፈለ/ ከኢትዮ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን/ በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  6. ተወካይ ከሆነ /ከሆነች ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያው የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ቫት ሳይጨምር በመሙላት በዘርፉ ድምር ከተሠራ በኋላ የቫት ድምር ለብቻ መቀመጥ አለበት፡፡
  9. ተጫራቾች የአንድ ዋጋ ከሞላ በኋላ ወደ ጎን አባዝቶ እና ወደ ታች ደምሮ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በእያንዳንዱ የዕቃ ዝርዝር በተናጠል ዝቀተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ እየሆነ ይመረጣል፡፡
  11. በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ስርዝ ድልዝ ካለ እና ፍሉድ ከተጠቀሙ ሰነዱ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቹ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ሲያቀርቡ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው መለየት ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጅናሉንና ፋይናንሽያሉን ለብቻ በማሸግ ኮፒውን ፋይናንሽያሉን ለብቻ በማሽግ እንዲሁም በየዘርፉ ከተራ ቁጥር 1-6 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ለብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግ በመጨረሻ ሶስቱንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ አሽጎ የሚወዳደርበትን ዘርፍ በመፃፍ ማቅረብ አለበት፡፡ በዚህ መሰረት ሶስቱንም ፖስታዎች ለየብቻ ሳያሽግ በአንድ ላይ አሽጎ ቢመጣ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ባቀረቡት ዋጋ ልክ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም C.PO ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  14. አሸናፊዎች ለውል ማስከበሪያ ካሽነፈው ጠቅላላ ዋጋ 10% ጥሬ ገንዘብ ወይም በC.P.O ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  15. የጨረታ ሰነዱን ከማሰልጠኛ ት/ቤቱ ፋይናንስ ዴስክ በሥራ ቀንና ሰዓት ከ 6/ 9/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 14/9/2017 ዓ.ም ድረስ የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነድ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  16. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በ15/9/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 7፡00 ሰዓት ድረስ በማ/ት/ቤቱ ቢሮ በር ላይ በሚዘጋጀው ሳጥን ሰነዱን ማስገባት አለባቸው፡፡ በዚሁ ቀን 15/ 9/ 2017 ዓ.ም ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በማ/ት/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 7፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
  17. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ማ/ት/ቤቱ በሚሰጠው የዕቃ አቅርቦት ትዕዛዝ መሰረት ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አሟልቶ ማቅረብ የሚችል እና በማ/ት/ቤቱ የጥራት ኮሚቴ ጥራቱን አረጋግጦ ማስረከብ አለበት፡፡ የጥራት ኮሚቴው ካልተቀበለው ቀይሮ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  18. አሸናፊ የሆነው ነጋዴ ክፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ ሕጋዊ ደረሰኝ ከካሽ ሬጅስተር ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
  19. ማ/ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
  20. ከአሸናፊው ተጫራች ማ/ት/ቤቱ በጀቱን በማረጋገጥ በዘርፉ 20% የመቀነስም ሆነ 20% የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
  21. በዚህ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ሌሎች ሕጎች በሀገሪቱ የግዥ አፈፃፀም መምሪያ መሰረት ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0587600018 በሥራ ሰዓት ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

 

ብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ት/ቤት

 

Save Tender