ድርጅታችን ደርባ ትራንስፖርት ኃ.የተ.የግ.ማ ደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግቢ ውስጥ የተለያዩ ያገለገሉ የከባድ ተሽከርካሪ ብዛት ከ3000 በላይ ጎማዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Derba Transport PLC (ደርባ ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግል ማህበር)
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ደርባ ትራንስፖርት ኃ.የተ.የግ.ማ ደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግቢ ውስጥ የተለያዩ ያገለገሉ የከባድ ተሽከርካሪ ብዛት ከ3000 በላይ ጎማዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ ተጫራቾች አስፈላጊውን ማስረጃ በማያያዝ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን የጎማዎቹን ሁኔታ ለማየት ደርባ ሲሚኒቶ ፋብሪካ ጊቢ ውስጥ በመምጣት ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ከ2፡30-6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30- 10:00 ሰዓት ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ዋናው መ/ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ በመምጣት የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፍል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚቻለው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ በ3ኛ ፎቅ ሰፕላይ ቢሮ ውስጥ በተዘጋጀው ሳጥን በማስገባት ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የመክፈቻው ቀን ለሥራ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፐኦ /CPO/ በድርጅታችን ስም በማዘጋጀት ዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የተያዘው ሲፒኦ /CPO/ አሸናፊ ለሚሆነው ተጫራች በዋጋው የሚታሰብለት ሲሆን ለተሸነፉት ግን ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡-
ከመስቀል አደባባይ ወደ ባንቢስ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ አጠገብ ያለው ድል ህንጻ
ስልክ ቁጥር፡ 0115539581
ደርባ ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግል ማህበር
